በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 6, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ሐና የተባለችው አውሎ ነፋስ ደቡብ ምሥራቃዊ ቴክሳስን መታች

ሐና የተባለችው አውሎ ነፋስ ደቡብ ምሥራቃዊ ቴክሳስን መታች

ቦታ

ቴክሳስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ

የደረሰው አደጋ

  • በእርከን 1 የምትመደበው ሐና የተባለችው አውሎ ነፋስ ሐምሌ 25, 2020 ቴክሳስን የመታች ሲሆን በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅና ኃይለኛ የባሕር ሞገድ እንዲከሰት አድርጋለች

  • ሐና በዚህ ዓመት በአትላንቲክ ውቅያኖስ ላይ ይከሰታሉ ተብለው ከሚጠበቁ አውሎ ነፋሶች መካከል የመጀመሪያዋ ናት

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ሁለት ወንድሞቻችን ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 193 አስፋፊዎች ለጊዜው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 347 የሚያህሉ የወንድሞቻችን ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 31 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር በመንፈሳዊና በሌሎች መስኮች ድጋፍ እያደረጉ ነው

“የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ወቅት በቴክሳስ ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እየረዳቸው ስላለ አመስጋኞች ነን።—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4