በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 1, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ሰደድ እሳት ምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስን እያመሰ ነው

ሰደድ እሳት ምዕራባዊ ዩናይትድ ስቴትስን እያመሰ ነው

ቦታ

ሰሜናዊ ካሊፎርኒያ እና ኦሪገን

የደረሰው አደጋ

  • 14,000 ገደማ በሚሆኑ መብረቆችና በሌሎች ምክንያቶች የተነሳ ከ700 የሚበልጡ ሰደድ እሳቶች ተነስተዋል፤ እሳቶቹ በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ እና በኦሪገን ከ400,000 ሄክታር የሚበልጥ መሬት አቃጥለዋል

  • ጭስ እና አመድ፣ አየሩ ለጤና በሚጎዳ መጠን እንዲበከል አድርጓል። በነሐሴ 21 በሰሜናዊ ካሊፎርኒያ የነበረው አየር ከየትኛውም የዓለም ክፍል የበለጠ የተበከለ እንደነበር ተገልጿል

  • ሁለቱ እሳቶች እስካሁንም እየነደዱ ሲሆን በካሊፎርኒያ ታሪክ ከተነሱት እሳቶች ሁሉ በትልቅነታቸው ሁለተኛና ሦስተኛ ደረጃ እንደያዙ ተዘግቧል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 936 አስፋፊዎች በጊዜያዊነት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 2 የወንድሞቻችን ቤቶች ወድመዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው የተጠቁትን ለመርዳት ጥረት እያደረጉ ነው

ወንድሞቻችንና እህቶቻችን የወንድማማች ማኅበሩ ላደረገላቸው እርዳታ ከፍተኛ አድናቆት አላቸው። አንድ ወንድም እንዲህ ብሏል፦ “ምንም ነገር ቢፈጠር ድርጅቱ ወዲያውኑ ይደርስልናል። ሁላችንም አንድ ቤተሰብ ነን።” እየተካሄደ ያለው የእርዳታ እንቅስቃሴ ማንኛውም ነገር “[ከአምላክ] ፍቅር ሊለየን እንደማይችል” የሚያሳይ ማስረጃ ነው።—ሮም 8:39