በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 24, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ሳሊ የተባለችው አውሎ ነፋስ በዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ምሥራቃዊ ክፍል ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለች

ሳሊ የተባለችው አውሎ ነፋስ በዩናይትድ ስቴትስ ደቡብ ምሥራቃዊ ክፍል ላይ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከተለች

ቦታ

አላባማ፣ ፍሎሪዳ እና ሚሲሲፒ

የደረሰው አደጋ

  • ዝግ ባለ ፍጥነት የምትጓዘው ሳሊ የተባለችው አውሎ ነፋስ መስከረም 16, 2020 አላባማን መታች። በጥቂት ሰዓታት ውስጥ የጣለው ከባድ ዝናብ ኃይለኛ ጎርፍ አስከትሏል

  • አውሎ ነፋሱ ንብረት ያወደመ ከመሆኑም ሌላ የኃይል መቋረጥ እንዲከሰት አድርጓል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 240 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 1 አስፋፊ ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶበታል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 143 ቤቶች እና 11 የስብሰባ አዳራሾች ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 12 ቤቶች እና 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • ሁለት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የአካባቢው የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጠቁት ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው፤ የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት መመሪያዎች በተከተለ መልኩ ነው

አንዲት አስፋፊ አውሎ ነፋሱ ከደረሰ በኋላ በጣም ተጨንቃ እንደነበረ ተናግራለች። ጉባኤዋ አፋጣኝ እርዳታ ካደረገላት በኋላ ግን በአድናቆት ስሜት “ወንድሞችና እህቶች ላሳዩኝ ፍቅርና ላደረጉልኝ ድጋፍ ከልብ አመሰግናለሁ” ብላለች።—1 ዮሐንስ 3:18