በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 23, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

ሴንት ሉዊስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሴንት ሉዊስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከነሐሴ 16-18, 2019

  • ቦታ፦ በሴንት ሉዊስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ዘ ዶም አት አሜሪካስ ሴንተር

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ እንግሊዝኛ፣ ክሮሽያኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 28,122

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 224

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ሰርቢያ፣ ስካንዲኔቪያ፣ ብሪታንያ፣ ቼክ ስሎቫክ፣ አርጀንቲና፣ አውስትራሌዢያ፣ ካናዳ፣ ክሮኤሺያ፣ ኮሎምቢያ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጃፓን፣ ፈረንሳይ፣ ፊሊፒንስ፣ ፊንላንድ፣ ፖላንድ፣ ፖርቱጋል

  • ተሞክሮ፦ የሜትሮሊንክ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ማርቲን ጉሌይ እንዲህ ብለዋል፦ “ሰዎች አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር እንደሚወዱ ይናገሩ ይሆናል። ፍቅራቸውን በተግባር ካላሳዩ ግን ይህ ፍቅር ሊባል አይችልም። እናንተ የይሖዋ ምሥክሮች ግን ፍቅርን የምታሳዩት በተግባር ነው። ትሑቶች ናችሁ፤ ደግሞም ፍቅር ሰዎችን ትሑት ያደርጋል እንጂ ኩራተኛ አያደርግም። እኔ የሜትሮሊንክ ሠራተኛ መሆኔ ባደረግኩት ባጅ ይታወቃል፤ እናንተ ደግሞ የይሖዋ ምሥክሮች መሆናችሁ በፍቅራችሁ ይታወቃል።”

    የባይ-ስቴት ዴቨሎፕመንት (በሴንት ሉዊስ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገትን ለማስፋፋት የሚሠራ የትራንስፖርት ድርጅት) የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ጄሪ ቫሊ ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦ “የምታስቡት ስለ ሥራው ብቻ ሳይሆን ስለ ሰዎችም ጭምር ነው። ዋነኛ ዓላማችሁ ሥራችሁን ማደራጀት ብቻ ሳይሆን እንግዶቻችሁን፣ አብረዋችሁ የሚሠሩትን የከተማው መስተዳድር ሠራተኞች እንዲሁም በሜትሮሊንክ የምንሠራውንም ጭምር የሚጠቅም ነገር ማከናወን ነው። አብረዋችሁ የሚሠሩ ሰዎች በሙሉ ሥራቸውን በደስታና በተሻለ መንገድ ማከናወን እንዲችሉ የቻላችሁትን ሁሉ ታደርጋላችሁ።”

 

የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች በሴንት ሉዊስ ላምበርት ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው የልዑካኑን መምጣት ሲጠባበቁ

ልዑካኑ ከአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ጋር በአደባባይ ምሥክርነት ሲካፈሉ

ወንድሞችና እህቶች ከስብሰባው በፊት አዳራሹን ሲያጸዱ

በስብሰባው ላይ ከተጠመቁት 224 ወንድሞችና እህቶች መካከል ሦስቱ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ዴቪድ ስፕሌን በስብሰባው ሦስተኛ ቀን የመደምደሚያውን ንግግር ሲያቀርብ

ልዑካኑ በፈገግታ ፕሮግራሙን ሲከታተሉ

እሁድ ቀን የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሜዳው ላይ ሆነው ተሰብሳቢዎቹን ሲሰናበቱ

ልዑካኑ ከአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ጋር ፎቶ ሲነሱ

ልዑካኑ በሴንት ሉዊስ መካነ አራዊት ውስጥ ያሉትን እንሰሳት ሲመለከቱ

ልዑካኑ በሴንት ሉዊስ የሕዝብ ቤተ መጻሕፍት ውስጥ፣ በ1611 የተዘጋጀውን በቀላሉ የማይገኝ የኪንግ ጄምስ ቨርዥን መጽሐፍ ቅዱስ ዋና እትም ሲመለከቱ፤ መጽሐፍ ቅዱሱ መዝሙር 83:18 ላይ ተገልጧል። ቤተ መጻሕፍቱ መጽሐፍ ቅዱሱ እዚህ ገጽ ላይ ተከፍቶ እንዲቀመጥ ያደረገው ለልዑካኑ ሲል ነው

ወጣት ወንድሞችና እህቶች ምሽት ላይ በተደረገው መዝናኛ ላይ ሲዘምሩ