በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 27, 2021
ዩናይትድ ስቴትስ

በሂላ ቤንድ፣ አሪዞና አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደረሰ

በሂላ ቤንድ፣ አሪዞና አውዳሚ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደረሰ

ነሐሴ 13, 2021 ሌሊት ላይ በአሪዞና እና በደቡባዊ ቴክሳስ በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ከባድ ዝናብ የጣለ ከመሆኑም ሌላ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል። አውዳሚ የሆነው ጎርፍ በተለይም በአሪዞና በሚገነው የሂላ ቤንድ ከተማ ላይ ከባድ ጉዳት አድርሷል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • የሚያሳዝነው በአደጋው 1 እህት ሕይወቷን አጥታለች

  • 5 የወንድሞቻችን ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 3 ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቹ እና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱት እረኝነት እያደረጉና ከመኖሪያቸው ለተፈናቀሉ አስፋፊዎች ጊዜያዊ ማረፊያ እያመቻቹ ነው

  • ሁሉም የእርዳታ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

በዚህ አደጋ ለተጎዱት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንጸልያለን። ይሖዋ ሕይወቷን ላጣችው እህታችን ቤተሰቦች መጽናኛ መስጠቱን እንዲቀጥል እንመኛለን።—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4