በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 17, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ የተነሳው ሰደድ እሳት እንደቀጠለ ነው

በምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስ የተነሳው ሰደድ እሳት እንደቀጠለ ነው

ቦታ

ካሊፎርኒያ፣ ኦሪገን እና ዋሺንግተን

የደረሰው አደጋ

  • በፍጥነት የሚጓዙት ሰደድ እሳቶች ከካሊፎርኒያ እስከ ዋሺንግተን ድረስ ከሁለት ሚሊዮን ሄክታር የሚበልጥ መሬት አቃጥለዋል

  • እሳቱ ለጤና ጎጂ በሆነ መጠን አየሩ እንዲበከል እያደረገ ነው

  • ከእሳቶቹ መካከል አንዱ በታሪክ ዘመናት በካሊፎርኒያ ከተነሱት እሳቶች ሁሉ ትልቁ ነው

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 4,546 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 61 ቤቶች ወድመዋል

  • 16 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ከወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ወንድሞችና እህቶችን እየረዱ ነው፤ የእርዳታ እንቅስቃሴው የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት መመሪያዎች በተከተለ መልኩ ነው

በአደጋው የተጠቁት ወንድሞች ይሖዋ በድርጅቱ በኩል ለሰጣቸው እርዳታ አመስጋኝ ናቸው። ቤቷ የወደመባት አንዲት እህት ወንድሞች ስለሰጧት እርዳታ ስትናገር “ምን እንደሚያስፈልገን እንኳ ከማወቃችን በፊት የሚያስፈልገንን ነገር ለማቅረብ ፈቃደኞች ነበሩ” ብላለች።

አደጋው በደረሰባቸው አካባቢዎች የሚኖሩት ወንድሞችና እህቶች አሁንም ችግር ውስጥ ቢሆኑም የይሖዋን ርኅራኄና ምሕረት ማየት ችለዋል።—ያዕቆብ 5:11