በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ወንድም ጆሴፍ ራዘርፎርድ መስከረም 10, 1922 በሴዳር ፖይንት፣ ኦሃዮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በተካሄደው ታሪካዊ ስብሰባ ላይ ንግግር ሲሰጥ። በስተ ቀኝ፦ ፕሮግራሙን ለመቅረጽ የተዘጋጀው የቪዲዮ ካሜራ

ሚያዝያ 11, 2022
ዩናይትድ ስቴትስ

ከቤተ መዘክራችን

በሴዳር ፖይንት የተካሄደውን ስብሰባ ቪዲዮ እየፈለግን ነው

በሴዳር ፖይንት የተካሄደውን ስብሰባ ቪዲዮ እየፈለግን ነው

በሴዳር ፖይንት የተካሄደውን ስብሰባ ቪዲዮ የሚያስተዋውቅ የጋዜጣ ማስታወቂያ

በ1922 በሴዳር ፖይንት፣ ኦሃዮ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተካሄደው ትልቅ ስብሰባ በይሖዋ ምሥክሮች ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ክንውን ነው፤ ምክንያቱም ወንድም ጆሴፍ ራዘርፎርድ “መንግሥቱን አስታውቁ” የሚለውን ጥሪ ያስተላለፈው በዚህ ስብሰባ ላይ ነበር።

ይሁንና ስብሰባው ታሪካዊ የሆነበት ሌላም ምክንያት አለ፤ ስብሰባው በቪዲዮ ተቀርጿል። ይሁንና እስካሁን ድረስ የቪዲዮውን ቅጂ ማግኘት አልተቻለም።

በመስከረም 1922 በተካሄደው በዚህ ብሔራት አቀፍ ስብሰባ ላይ የተነሳ አንድ ፎቶግራፍ እንደሚያሳየው ይህን ታሪካዊ ስብሰባ ለመቅረጽ የተዘጋጀ የቪዲዮ ካሜራ አነስተኛ መድረክ ላይ ተቀምጦ ነበር። በወቅቱ ፊልም ገና አዲስ ቴክኖሎጂ ነበር።

የስብሰባው ቪዲዮ ብዙ ሰዎች እጅ ደርሶ የነበረ ይመስላል። ለምሳሌ አንድ ጋዜጣ ቪዲዮውን የሚያስተዋውቅ ማስታወቂያ ይዞ ወጥቶ ነበር። ማስታወቂያው “ስብሰባውን ከቤታችሁ ተመልከቱ። ወዳጆቻችሁንና የጥምቀት ሥነ ሥርዓቱን እዩ” ይላል። በተጨማሪም ማስታወቂያው ለሌሎች ለመመሥከር የሚያስችል ምክር ይዟል፤ እንዲህ ይላል፦ “የስብሰባውን ቪዲዮ ለጎረቤቶቻችሁ በማሳየት ምሥክርነት ስጧቸው። አሁኑኑ እዘዙ።”

የዚህ ቪዲዮ ቅጂ የሚገኝበትን ካወቃችሁ እባካችሁ ወደ MuseumDonations@jw.org በመጻፍ የቤተ መዘክር ክፍሉን አነጋግሩ፤ ወይም በሚከተለው አድራሻ ተጠቅማችሁ ለይሖዋ ምሥክሮች ዋና መሥሪያ ቤት መጻፍ ትችላላችሁ፦ 1 Kings Drive, Tuxedo Park, NY 10987። ይህን የቲኦክራሲያዊ ታሪካችንን ውድ ቅርስ እንደምናገኝ ተስፋ እናደርጋለን።