ሰኔ 4, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ
በቨርጂኒያ ቢች፣ ዩናይትድ ስቴትስ የደረሰ የተኩስ ጥቃት
ግንቦት 31, 2019 መሣሪያ የታጠቀ አንድ ሰው በቨርጂኒያ ቢች፣ ቨርጂኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኝ ማዘጋጃ ቤት ውስጥ በሚሠሩ ሠራተኞች ላይ የተኩስ ጥቃት ሰነዘረ። በጥቃቱ 12 ሰዎች የሞቱ ሲሆን አራቱ ደግሞ ቆስለዋል።
የሚያሳዝነው ነገር የዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ሪፖርት እንዳደረገው ላኪታ ብራውን የተባለች እህታችን በጥቃቱ ሕይወቷን አጥታለች። እህት ብራውን ዕድሜዋ 39 ዓመት ሲሆን በኖርፎክ፣ ቨርጂኒያ በሚገኘው ሲቪው ፈረንሳይኛ ጉባኤ ውስጥ በዘወትር አቅኚነት ታገለግል ነበር። የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኛ ሆናም አገልግላለች። የጉባኤው ሽማግሌዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቹ ለእህት ብራውን ወዳጆችና ቤተሰቦች ቅዱስ ጽሑፋዊ ማበረታቻና ማጽናኛ እየሰጡ ነው።
እህታችንን በሞት በማጣታችን በእጅጉ አዝነናል። እንዲህ ያሉ አሰቃቂ አደጋዎች የሚያበቁበትንና በምድር ላይ “ብዙ ሰላም” የሚኖርበትን ጊዜ እንናፍቃለን።—መዝሙር 37:10, 11