በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 19, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካሊፎርኒያ ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ የተከፈተ ተኩስ

በዩናይትድ ስቴትስ፣ ካሊፎርኒያ ባለ ትምህርት ቤት ውስጥ የተከፈተ ተኩስ

ኅዳር 14, 2019 በሳንታ ክላሪታ፣ ካሊፎርኒያ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ አንድ ተማሪ አብረውት በሚማሩ ልጆች ላይ ተኩስ ከፈተ። ጥቃት ፈጻሚው፣ ተኩስ ከፍቶ ሁለት ተማሪዎችን ከገደለና ሦስት ተማሪዎችን ካቆሰለ በኋላ በራሱ ላይ ተኩሷል።

የሚያሳዝነው የአንዲት እህታችን ልጅ የሆነ ዶሚኒክ ብላክዌል የተባለ ወጣት በዚህ ጥቃት የተነሳ ሕይወቱ አልፏል። ይህ ልጅ የ14 ዓመት ወጣት ሲሆን እናቱ ከሆነችው ከእህት ናንሲ ብላክዌል ጋር አዘውትሮ በስብሰባ ላይ ይገኝ ነበር። የዶሚኒክ አባትና እናት በሕይወት ያሉ ሲሆን ሦስት ትናንሽ ወንድሞች አሉት። ሽማግሌዎች ለቤተሰቡም ሆነ ለጉባኤው መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማጽናኛና ድጋፍ ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው።

ይህ ዜና በጥልቅ አሳዝኖናል። ሆኖም አምላክ ‘እንባን ሁሉ የሚያብስበትን’ እንዲሁም ‘ሞት፣ ሐዘን፣ ጩኸትና ሥቃይ የማይኖርበትን’ ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—ራእይ 21:4