በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት የተሰነጠቀ መሬት

ሐምሌ 15, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ

በደቡባዊ ካሊፎርኒያ የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ

ከሐምሌ 4, 2019 አንስቶ በደቡባዊ ካሊፎርኒያ በሚገኘው የሞሃቪ በረሃ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጦች የደረሱ ሲሆን ነውጡን ተከትለው የተከሰቱ ንዝረቶችም ነበሩ። ከእነዚህ መካከል በሬክተር ስኬል መለኪያ 7.1 የተመዘገበ ነውጥ ይገኝበታል፤ ይህም ባለፉት 20 ዓመታት ውስጥ በዚህ አካባቢ ከደረሱት ከፍተኛ ርዕደ መሬቶች አንዱ ነው።

አደጋው የደረሰው በሪጅክረስት ከተማ አቅራቢያ ነው፤ በዚህች ከተማ ውስጥ 215 አስፋፊዎች ይኖራሉ። ደስ የሚለው ከወንድሞቻችን መካከል በአደጋው የከፋ ጉዳት የደረሰበት የለም። ሆኖም ሦስት አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ሰባት አስፋፊዎች ደግሞ ከመኖሪያቸው እንደተፈናቀሉ መጀመሪያ የተጠናቀረው ሪፖርት ያሳያል። ከዚህም ሌላ ከወንድሞቻችን መኖሪያ ቤቶች መካከል 7ቱ ወድመዋል እንዲሁም 35ቱ ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የስብሰባ አዳራሾች መለስተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

በአካባቢው የሚደረገውን የእርዳታ ሥራ ሁለት የወረዳ የበላይ ተመልካቾች እያደራጁ ነው። እንዲሁም የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በመሬት መንቀጥቀጡ ለተጎዱ ወንድሞችና እህቶች እረኝነት እያደረጉ ነው።

ይሖዋ፣ እንዲህ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ሲደርሱ ፈተናውን ለመቋቋም የሚያስችል ጥበብ ለእምነት ባልንጀሮቻችንን ምንጊዜም እንዲሰጥ እንጸልያለን።—ምሳሌ 2:6-8