በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መኪኒ፣ ቴክሳስ ከአደጋው በኋላ ከላይ ሲታይ

መጋቢት 1, 2021
ዩናይትድ ስቴትስ

በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተው ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ቅዝቃዜ ከ7,500 በላይ ሰዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቀለ

በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተው ታይቶ የማይታወቅ ከባድ ቅዝቃዜ ከ7,500 በላይ ሰዎችን ከመኖሪያቸው አፈናቀለ

ቦታ

የዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ግዛቶች

የደረሰው አደጋ

  • ከየካቲት 13, 2021 ጀምሮ የዩናይትድ ስቴትስ ደቡባዊ ክፍሎች በኃይለኛ ቅዝቃዜ ተመትተዋል። ከፍተኛ ጉዳት የደረሰው በቴክሳስ ነው። በረዶ ሲጥል በተከሰተው ታይቶ የማይታወቅ ከፍተኛ ቅዝቃዜ ምክንያት በመኖሪያ ቤቶችና በንግድ ቤቶች ለቀናት ያህል የኃይል መቋረጥ ተከስቷል፤ ቅዝቃዜው በብዙ ቦታዎች በውኃ መተላለፊያ ቱቦዎች ውስጥ የበረዶ ግግር እንዲፈጠር አድርጓል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 11 አስፋፊዎች ሆስፒታል መግባት አስፈልጓቸዋል

  • 94 አስፋፊዎች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 7,650 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 14 የስብሰባ አዳራሾች እና 1 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 5 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 3,224 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 113 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 12 ቤቶች ፈርሰዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአካባቢው ካለው የኮቪድ-19 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ጋር በመሆን አስፈላጊውን እርዳታ እያደረጉ ነው፤ የእርዳታ ሥራው ንጹሕ የመጠጥ ውኃ ማቅረብን እንዲሁም ጉዳት ለደረሰባቸው መኖሪያ ቤቶች እና የስብሰባ አዳራሾች ጊዜያዊ ጥገና ማድረግን ይጨምራል። በአደጋው ምክንያት ከቤታቸው የተፈናቀሉት አስፋፊዎች ጊዜያዊ ማረፊያ እንዲያገኙም ተደርጓል። የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይሖዋ እንዲህ ባለው መጥፎ የአየር ጠባይ ጉዳት የደረሰባቸውን ወንድሞች ስለሚያጽናና እናመሰግነዋለን።—2 ቆሮንቶስ 1:3