በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መኪኖች በሂውስተን፣ ቴክሳስ በሚገኝ ትልቅ መንገድ ላይ ያለሹፌር ተትተው

ጥቅምት 2, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

በደቡብ ምሥራቅ ቴክሳስ የተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ

በደቡብ ምሥራቅ ቴክሳስ የተከሰተ የጎርፍ መጥለቅለቅ

ከመስከረም 16, 2019 አንስቶ በነበሩት ተከታታይ ቀናት ኢሜልዳ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ 102 ሴንቲ ሜትር ዝናብ እንዲጥል በማድረጉ ሳቢያ የደቡብ ምሥራቅ ቴክሳስ የተወሰኑ ክፍሎች በጎርፍ ተጥለቀለቁ። ይህ አውሎ ነፋስ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ከባድ ዝናብ ካስከተሉ አውሎ ነፋሶች መካከል ይመደባል። ከጎርፍ መጥለቅለቁ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ መኪኖች በመንገድ ላይ የተተዉ ሲሆን በርካታ ሰዎች ከመኖሪያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል።

ከዩናይትድ ስቴትስ ቅርንጫፍ ቢሮ ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው አደጋው በደረሰበት አካባቢ ከሚኖሩት 29,649 ወንድሞች መካከል አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ወይም ሕይወቱ ያለፈ የይሖዋ ምሥክር የለም። ሆኖም 114 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። በተጨማሪም 145 የወንድሞቻችን ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አሥር የስብሰባ አዳራሾችም ተጎድተዋል።

ቅርንጫፍ ቢሮው የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ያቋቋመ ሲሆን ኮሚቴው የጉዳቱን መጠን ለማወቅና የእርዳታ ሥራውን ለማደራጀት ከአካባቢው የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከሽማግሌዎች ጋር በቅርበት እየሠራ ይገኛል። ‘ታማኝ ፍቅሩ እስከ ሰማያት የሚደርሰው’ አምላካችን ይሖዋ ወንድሞቻችንን እንደሚደግፍ እንተማመናለን።—መዝሙር 36:5