በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሃርሊንገን፣ ቴክሳስ በወንድሞች ቤት ደጃፍ ላይ በጎርፍ የተጥለቀለቁ መኪኖች

ሐምሌ 10, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ

በደቡብ ቴክሳስ ያጋጠመ አውሎ ነፋስና ጎርፍ

በደቡብ ቴክሳስ ያጋጠመ አውሎ ነፋስና ጎርፍ

ሰኔ 24, 2019 ደቡብ ቴክሳስ በአውሎ ነፋስና በጎርፍ ተመታ። የመገናኛ ብዙኃን እንደገለጹት በመቶዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የተጥለቀለቁ ሲሆን ከ100 የሚበልጡ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

በአደጋው ምክንያት የከፋ ጉዳት የደረሰበት አስፋፊ ባይኖርም 47 ወንድሞችና እህቶች መኖሪያቸውን ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። ከዚህም በተጨማሪ አውሎ ነፋሱ ወንድሞቻችን በሚኖሩባቸው 65 ቤቶችና ከስብሰባ አዳራሹ ጋር ተያይዞ በተሠራ መኖሪያ ቤት ላይ ጉዳት አድርሷል።

የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱት ወንድሞች እረኝነት እያደረጉ ነው። በተጨማሪም የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው ለተፈናቀሉት ወንድሞች መኖሪያ የማመቻቸቱን እንዲሁም ምግብ፣ ውኃና ልብስ የማከፋፈሉን ሥራ እያደራጀ ነው። ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶችና በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ የሚገኘውን ቤት ለማጽዳትና ለመጠገን ጥረት እየተደረገ ነው።

በደቡብ ቴክሳስ የሚኖሩ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መደገፋችንን እንቀጥላለን፤ በይሖዋ በመታመን ይህን ሁኔታ ተቋቁመው እንደሚጸኑ እንተማመናለን።—ኢሳይያስ 26:3, 4