በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ዩናይትድ ስቴትስ

ታሪካዊ እመርታዎች በዩናይትድ ስቴትስ

ታሪካዊ እመርታዎች በዩናይትድ ስቴትስ
  1. ሰኔ 17, 2002—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የይሖዋ ምሥክሮች እምነታቸውን በይፋ የማወጅ ሕገ መንግሥታዊ መብት እንዳላቸው ያረጋገጠውን በ1940ዎቹ ዓመታት ያስተላለፈውን ውሳኔ በድጋሚ አጸና (ከሳሽ ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ኒው ዮርክ እና ተከሳሽ የስትራተን መንደር)

  2. ነሐሴ 1998—የይሖዋ ምሥክሮች ብዛት ከአንድ ሚሊዮን አለፈ

  3. ሚያዝያ 15, 1992—የኦሃዮ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የታችኛው ፍርድ ቤት የወላጅን ሃይማኖት መሠረት በማድረግ የአሳዳጊነት መብትን ማገድ እንደማይችል በመግለጽ የከፍተኛ ፍርድ ቤቱን ውሳኔ አጽንቷል

  4. ጥቅምት 30, 1985—የሚሲሲፒ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ ለሕክምና ደም ያለመውሰድ መብት በግለሰቦች የግላዊነት እና በነፃነት የማምለክ መብት ከለላ ሥር እንደሆነ አረጋገጠ (ኢን ሬ ብራውን)

  5. ነሐሴ 31, 1972—የኮሎምቢያ አውራጃ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት፣ መንግሥት አንድ አዋቂ ሰው ለሕክምና ደም ላለመውሰድ ያደረገውን ውሳኔ ሊያከብር እንደሚገባ ወሰነ (ኢን ሬ ኦዝቦርን)

  6. ኅዳር 30, 1953—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሙሉ ጊዜ አገልጋይ የሆነ አንድ የይሖዋ ምሥክር ዓለማዊ ሥራ የሚሠራ ቢሆንም እንኳ ከወታደራዊ አገልግሎት ነፃ ለመሆን ያቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሊሆን እንደማይገባ ወሰነ (ከሳሽ ዲኪንሰን እና ተከሳሽ ዩናይትድ ስቴትስ)

  7. 1944—በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሚደርሰው ስደት ጋብ አለ

  8. ሰኔ 14, 1943—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በተከሳሽ ጎባይትስ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ቀለበሰ፤ ለባንዲራ ሰላምታ መስጠትን አስገዳጅ የሚያደርግ ሕግ የይሖዋ ምሥክር ተማሪዎችን የንግግር እና የሃይማኖት መብት እንደሚጋፋ ወሰነ (ከሳሽ ዌስት ቨርጂኒያ የትምህርት ቢሮ እና ተከሳሽ በርኔት)

  9. ግንቦት 3, 1943—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ሃይማኖታዊ ጽሑፎች ለማሰራጨት የሚያስፈልጋቸውን ፈቃድ በክፍያ እንዲያገኙ የሚጠይቀውን ደንብ ሻረ (ከሳሽ መርዶክ እና ተከሳሽ ፔንስልቬንያ)

  10. ሰኔ 3, 1940—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የሕዝብ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ለባንዲራ ሰላምታ እንዲሰጡ የሚያስገድደውን ደንብ አጸና፤ (ከሳሽ ሚነርስቪል ትምህርት ቤት እና ተከሳሽ ጎባይትስ) ይህን ተከትሎም በይሖዋ ምሥክሮች ላይ ስደት ተቀሰቀሰ

  11. ግንቦት 20, 1940—የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የየአካባቢውም ሆነ የየግዛቱ ባለሥልጣናት የሃይማኖት ነፃነትን የሚደነግገውን ሕግ እንዲያስከብሩ ለመጀመሪያ ጊዜ ውሳኔ አሳለፈ። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች ስብከት ሰላም እንደማያደፈርስ ገለጸ (ከሳሽ ካንትዌል እና ተከሳሽ ከኔቲከት)

  12. መጋቢት 28, 1938—የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የይሖዋ ምሥክሮች ያለፈቃድ ጽሑፍ እንዳያሰራጩ የሚከለክለውን ደንብ ሻረ (ከሳሽ ሎቬል እና ተከሳሽ የግሪፊን ከተማ)

  13. ሐምሌ 26, 1931—የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች፣ የይሖዋ ምሥክሮች በሚል ስም መጠራት ጀመሩ

  14. ግንቦት 14, 1919—በሕጋዊ ማኅበሩ ዋነኛ አባላት ላይ የተላለፈው የጥፋተኝነት ብይን ተሻረ፤ ቆየት ብሎም ሙሉ በሙሉ ከክስ ነፃ ተደረጉ

  15. ሰኔ 20, 1918—ዋና ዋና የሚባሉ የሕጋዊ ማኅበሩ አባላት፣ ‘የጦርነት ቅስቀሳውን የሚጻረር ጽሑፍ አሳትማችኋል’ በሚል ክስ ጥፋተኛ ተብለው ታሰሩ

  16. መጋቢት 4, 1909—በኋላ ላይ ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ኒው ዮርክ ተብሎ የተሰየመው ፒፕልስ ፑልፒት አሶሲዬሽን የተሰኘው ሕጋዊ ማኅበር ተቋቋመ

  17. ጥር 31, 1909—የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ዋና መሥሪያ ቤታቸውን ወደ ብሩክሊን፣ ኒው ዮርክ አዛወሩ

  18. ታኅሣሥ 15, 1884—በኋላ ላይ ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ ኦቭ ፔንስልቬንያ የሚል ስያሜ ያገኘው ሕጋዊ ማኅበር ተቋቋመ

  19. 1880ዎቹ—የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች አሌጌኒ፣ ፔንስልቬንያ ውስጥ ዋና መሥሪያ ቤታቸውን ከፈቱ

  20. ሐምሌ 1879—አሁን መጠበቂያ ግንብ ተብሎ የሚጠራው መጽሔት የመጀመሪያ እትም ወጣ

  21. 1870—ቻርልስ ቴዝ ራስል እና ተባባሪዎቹ አሌጌኒ፣ ፔንስልቬንያ ውስጥ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ቡድን አቋቋሙ፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች የሚል ስያሜም አገኙ