በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተው ዝናብ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል

ጥር 19, 2023
ዩናይትድ ስቴትስ

ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስን መታ

ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትስን መታ

የዩናይትድ ስቴትስ ግዛት የሆነችው ካሊፎርኒያ ከጥር 4, 2023 አንስቶ በከባድ በረዶ፣ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስ ተመታለች። የማያባራውን ዝናብ ተከትሎ ጎርፍ፣ የመሬት መንሸራተትና የኃይል መቆራረጥ ተከስቷል። ሺዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ ቢያንስ 19 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአንዳንድ አካባቢዎች በጥቂት ቀናት ውስጥ የጣለው ኃይለኛ ዝናብ በዓመት ከሚያገኙት የዝናብ መጠን ከግማሽ በላይ ነው።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • በአደጋው የሞተ የይሖዋ ምሥክር የለም

  • 199 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 4 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 141 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 23 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የርቀት የትርጉም ቢሮ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች፣ ጉዳት ለደረሰባቸው ቤተሰቦች እረኝነት እያደረጉና ተግባራዊ እገዛ እየሰጡ ነው

  • 44 ቤቶች መለስተኛ ጥገና ተደርጎላቸው ለመኖሪያነት ምቹ ሆነዋል

  • 15 ቤቶች ታድሰዋል

በዚህ የጭንቅ ቀን ይሖዋ ወንድሞቻችንን እንደሚያጽናናቸው እንተማመናለን።​—መዝሙር 50:15