ግንቦት 29, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ
አትላንታ፣ ዩናይትድ ስቴትስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከግንቦት 17-19, 2019
ቦታ፦ መርሰዲስ ቤንዝ ስታዲየም፣ አትላንታ፣ ጆርጂያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ
ፕሮግራሙ የተካሄደባቸው ቋንቋዎች፦ አማርኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ሩሲያኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 46,374
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 314
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሆንግ ኮንግ፣ ሩማኒያ፣ ስካንዲኔቪያ፣ብሪታንያ፣ ብራዚል፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ቺሊ፣ ኔዘርላንድስ፣ አውስትራሌዢያ፣ ኢትዮጵያ፣ እስራኤል፣ ካናዳ፣ ካዛክስታን፣ ኮሎምቢያ፣ ጃፓን፣ ግሪክ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ፖርቱጋል
በ2019 የሚደረጉትን ብሔራት አቀፍ ስብሰባዎች በተመለከተ jw.org ላይ ዜና በሚለው ዓምድ ሥር ከሚወጡት ስብሰባውን የሚያስቃኙ 24 ርዕሶች እና የፎቶግራፍ ስብስቦች መካከል ይህ የመጀመሪያው ነው።
የተወሰኑ የይሖዋ ምሥክሮች ከስታዲየሙ ውጭ ሆነው ፎቶግራፍ ሲነሱ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ስቲቨን ሌት የቅዳሜውን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ
ለጥምቀት ከተዘጋጁት ሁለት ገንዳዎች በአንዱ ላይ ወንድሞች ሲያጠምቁ
ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ላይ የቀረቡትን ንግግሮች ሲያዳምጡ
ከሌሎች አገሮች ከመጡት 164 የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች መካከል የተወሰኑት እሁድ ዕለት በስብሰባው መደምደሚያ ላይ በመርሰዲስ ቤንዝ ስታዲየም ሜዳ ላይ
ልዑካኑ በአካባቢው ካሉ ወንድሞችና እህቶች ጋር አገልግሎት ወጥተው
ባሕላዊ ልብስ የለበሱ ልዑካን ፎቶግራፍ ሲነሱ
ትናንሽ ልጆች “ቀኑ በጣም ቀርቧል፤ ገነት ውስጥ እንገናኝ” የሚል ማስታወቂያ ይዘው ልዑካኑን ሲሸኙ
በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ልዑካኑ የኢትዮጵያን ባሕላዊ ልብስ ለብሰው
እንግዶቹን ለመቀበል ከተደረጉት ዝግጅቶች በአንዱ ማብቂያ ላይ መድረክ ላይ የነበሩት ወንድሞች ለአድማጮች እጃቸውን ሲያውለበልቡ፤ ከጀርባቸው “እንወዳችኋለን!” የሚል ጽሑፍ ይታያል