በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 8, 2021
ዩናይትድ ስቴትስ

አይዳ የተባለችው አውሎ ነፋስ በደቡባዊና በሰሜናዊ ዩናይትድ ስቴትስ ውድመት አስከተለች

አይዳ የተባለችው አውሎ ነፋስ በደቡባዊና በሰሜናዊ ዩናይትድ ስቴትስ ውድመት አስከተለች

ነሐሴ 29, 2021 አይዳ የተባለችው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በፖርት ፉርሾን፣ ሉዊዚያና አቅራቢያ የሚገኘውን የባሕር ዳርቻ መታች። አይዳ በባሕሩ ዳርቻ የውኃው ከፍታ እንዲጨምር ያደረገች ከመሆኑም ሌላ ኃይለኛ ዝናብና ነፋስ አስከትላለች። በዚህም የተነሳ የጎርፍ መጥለቅለቅ ደርሷል፤ በርካታ ሕንፃዎች ወድመዋል፤ እንዲሁም የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጣል። መስከረም 1 በአውሎ ነፋሱና በአካባቢው የአየር ሁኔታ የተነሳ በሰሜን ምሥራቅ ዩናይትድ ስቴትስ ከባድ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል። በአንዳንድ ቦታዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እስኪመለስ ድረስ ሳምንታት ሊወስድ እንደሚችል ይጠበቃል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • እስካሁን ባለን መረጃ መሠረት በአደጋው ሕይወቱን ያጣ የይሖዋ ምሥክር የለም

  • 2 ወንድሞች መጠነኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 እህት ከቤቷ ለመሸሽ ጥረት በምታደርግበት ወቅት በደረሰባት ጉዳት ሆስፒታል ገብታለች

  • 1,429 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 183 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 19 ቤቶች ወድመዋል

  • 43 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 10 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 4 የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

በአውሎ ነፋሱ ጉዳት የደረሰበት በኒው ኦርሊየንስ፣ ሉዊዚያና የሚገኝ የአንዲት እህት ቤት

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • በአካባቢው ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች እንዲሁም የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በአደጋው ለተጎዱት ወንድሞችና እህቶች እረኝነት እያደረጉ ነው

  • አስቸኳይ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ወንድሞች የእርዳታ ቁሳቁስ እየተከፋፈለ ነው

  • ሁሉም የእርዳታ እንቅስቃሴዎች የሚካሄዱት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ወንድሞቻችን ለአደጋ ለመዘጋጀት ያደረጉት ጥረትና መንግሥት ያወጣውን መመሪያ ተከትለው አካባቢውን ለቀው መሄዳቸው የብዙዎችን ሕይወት ለማትረፍ አስችሏል።—ምሳሌ 22:3