በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 14, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ኢሳይያስ የተባለው አውሎ ነፋስ በምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

ኢሳይያስ የተባለው አውሎ ነፋስ በምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አደረሰ

ቦታ

ምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ

የደረሰው አደጋ

  • በእርከን 1 የሚመደበው ኢሳይያስ የተባለው አውሎ ነፋስ ነሐሴ 3, 2020 ኖርዝ ካሮላይናን መታ

  • አውሎ ነፋሱ ምሥራቃዊውን የባሕር ዳርቻ ተከትሎ ወደ ላይ ሲሄድ መጠነ ሰፊ ጉዳት ያስከተለ ከመሆኑም ሌላ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ አድርጓል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • አንዲት እህት ጉዳት ደርሶባታል

  • 12 ቤተሰቦች ለጊዜው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 55 የሚያህሉ የወንድሞቻችን ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • አምስት ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • በርካታ ተሽከርካሪዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • አምስት የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች የኮቪድ-19 የደህንነት መርሆችን ሳይጥሱ ወዲያውኑ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ለመርዳት ጥረት አድርገዋል

ይሖዋ በእነዚህ ከባድ የተፈጥሮ አደጋዎች የተጎዱ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እየረዳቸው ስለሆነ ደስተኞች ነን። ሁሉም ሰው እንዲህ ባሉ አደጋዎች ምክንያት “መከራ ይደርስብኛል” ከሚለው ስጋት ነፃ የሚሆንበትን ጊዜ በጉጉት እንጠብቃለን።—ምሳሌ 1:33