በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰተውን ዲክሲ የተባለ ሰደድ እሳት የሚያሳይ የምሽት ፎቶግራፍ

ነሐሴ 16, 2021
ዩናይትድ ስቴትስ

ካሊፎርኒያ በሰደድ እሳቶች እየታመሰች ነው

ካሊፎርኒያ በሰደድ እሳቶች እየታመሰች ነው

በካሊፎርኒያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ የተከሰቱት በርካታ ሰደድ እሳቶች መጠነ ሰፊ ጉዳት አስከትለዋል። ከእነዚህ መካከል ትልቁ ዲክሲ የተባለው ሰደድ እሳት ሲሆን እስካሁን 187,562 ሄክታር መሬት አውድሟል። ዲክሲ በካሊፎርኒያ ታሪክ እስካሁን ከደረሱት ሰደድ እሳቶች በስፋቱ ሁለተኛው ነው።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 415 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 17 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

  • 2 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • አደጋው በደረሰበት አካባቢ ያሉት የወረዳ የበላይ ተመልካቾች ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ እየሰጡ ነው፤ ይህም ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ አስፋፊዎች ጊዜያዊ መኖሪያ እንዲያገኙ ማመቻቸትን ይጨምራል

  • ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

የይሖዋ ሕዝቦች መከራ በሚያጋጥማቸው ጊዜም ጭምር ወንድሞቻቸውንና እህቶቻቸውን ለመርዳት ራሳቸውን በማቅረብ እውነተኛ ወዳጆች መሆናቸውን ያሳያሉ።—ምሳሌ 17:17