በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኅዳር 6, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ

ዚታ የተባለው አውሎ ነፋስ ደቡብ ምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስን መታ

ዚታ የተባለው አውሎ ነፋስ ደቡብ ምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስን መታ

ቦታ

ደቡብ ምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ

የደረሰው አደጋ

  • በእርከን 2 የሚመደበውና በፍጥነት የሚጓዘው አውሎ ነፋስ ጥቅምት 28, 2020 ሉዊዚያናን መታ፤ ከዚያም ኃይሉን ቀንሶ በደቡብ ምሥራቃዊ ዩናይትድ ስቴትስ በሚገኙ ሌሎች ቦታዎች ላይ ጉዳት አደረሰ

  • በባሕር ዳርቻዎች አካባቢ የተከሰተው ጎርፍና ኃይለኛ ነፋስ በንብረት ላይ ጉዳት ያደረሰ ከመሆኑም ሌላ በብዙ ቦታዎች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጥ አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 324 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 1 አስፋፊ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶበታል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 291 ቤቶችና 14 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 8 ቤቶችና 3 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 ቤት ሙሉ በሙሉ ወድሟል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የጉባኤ ሽማግሌዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ማበረታቻና ቁሳዊ እርዳታ እየሰጡ ነው። ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ እና ሎራ ከተባለችው አውሎ ነፋስ ጋር በተያያዘ የተቋቋሙት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ዚታ በተባለው አውሎ ነፋስ ለተጎዱት ወንድሞችና እህቶችም እርዳታ እያበረከቱ ነው፤ ይህን እያደረጉ ያሉት ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ሳይጥሱ ነው።

ይህ አውሎ ነፋስ በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ላይ ጉዳት ማስከተሉን በመስማታችን አዝነናል። በዚህ ወቅትም ቢሆን ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ያለው ታማኝ ፍቅር የወንድማማች ማኅበራችን በሚያከናውነው የእርዳታ ሥራ አማካኝነት ታይቷል።—መዝሙር 89:1