ጥቅምት 19, 2020
ዩናይትድ ስቴትስ
ዴልታ የተባለው አውሎ ነፋስ በሉዊዚያና ከባድ ጉዳት አስከትሏል
ቦታ
ሉዊዚያና እና ደቡባዊ ምሥራቅ ቴክሳስ
የደረሰው አደጋ
በእርከን 2 የሚመደበው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ጥቅምት 9, 2020 ላይ ደቡባዊ ምዕራብ ሉዊዚያናን የመታ ሲሆን በቅርቡ ሎራ በተባለችው አውሎ ነፋስ በተመቱ አካባቢዎች ላይ ተጨማሪ ጉዳት አስከትሏል
ከባድ ዝናብ የቀላቀለው ይህ አውሎ ነፋስ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያስከተለ ከመሆኑም ሌላ በበርካታ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል
በወንድሞቻችን እና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
1,583 የሚያህሉ አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
216 ቤቶችና 16 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
7 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
3 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ፈርሰዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ምግብ፣ ውኃ፣ መጠለያና ሌሎች ነገሮች የሚያስፈልጓቸውን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን እየረዱ ነው። የእርዳታ እንቅስቃሴውን እያስተባበረ ያለው ሎራ የተባለችውን አውሎ ነፋስ ተከትሎ የተቋቋመው የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ነው። ወንድሞቻችን ከኮቪድ-19 ጋር የተያያዙ የደህንነት መመሪያዎችን ሳይዘነጉ በትጋት እየሠሩ ነው
በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ለወንድሞች መንፈሳዊ ድጋፍ ለመስጠትም ጥረት እያደረጉ ነው። አንድ የጉባኤ ሽማግሌ የተመለከተውን ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “ይሖዋ ለእነዚህ ወንድሞችና እህቶች እየሰጣቸው ያለውን ጥንካሬ ማየት በጣም ያስገርማል። ‘ከሰብዓዊ ኃይል በላይ የሆነ ኃይል’ እንደሰጣቸው ምንም አያጠራጥርም።”—2 ቆሮንቶስ 4:7
ይሖዋ በእነዚህ አውሎ ነፋሶች ጉዳት ለደረሰባቸው ውድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን “መጠጊያና መሸሸጊያ” ስለሆናቸው በጣም እናመሰግነዋለን።—ኢሳይያስ 4:6