ነሐሴ 15, 2019
ዩናይትድ ስቴትስ
ፊኒክስ፣ ዩናይትድ ስቴትስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከነሐሴ 9-11, 2019
ቦታ፦ በፊኒክስ፣ አሪዞና፣ ዩናይትድ ስቴትስ የሚገኘው ቼዝ ፊልድ
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ እንግሊዝኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 40,237
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 352
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሕንድ፣ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ማይክሮኔዥያ፣ ስሪ ላንካ፣ ስካንዲኔቪያ፣ ብሪታንያ፣ ቱርክ፣ ታሂቲ፣ ታይላንድ፣ ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ፣ ቺሊ፣ አውስትራሌዢያ፣ ካናዳ፣ ኮሪያ፣ ግሪክ፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ
ተሞክሮ፦ በፊኒክስ ውስጥ ስብሰባዎችን የማደራጀትና ሆቴሎች የመያዝ ሥራ የሚያከናውነው ቪዚት ፊኒክስ የተባለው ኩባንያ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ስቲቭ ሙር እንዲህ ብለዋል፦ “ረጅም ጊዜ በዚህ ሥራ ተካፍያለሁ፤ የዚህኛውን ያህል በደንብ የተደራጀ ስብሰባ ገጥሞኝ አያውቅም። በሥራው በጣም ተደስቻለሁ። በዚያ ላይ ደግሞ ስትጨርሱ ስታዲየሙን እንደምታጸዱ ቃል ገብታችኋል፤ እንዲህ የሚያደርግ ሌላ ማንም የለም።”
ከዓለም ዙሪያ የመጡ ልዑካን በፊኒክስ ስካይ ሃርበር ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሞቅ ያለ አቀባበል ሲደረግላቸው
በፊኒክስ የሚኖሩ ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑ ወደ ሆቴል በሚመጡበት ጊዜ አቀባበል ሊያደርጉላቸው ተዘጋጅተው
በመቶዎች የሚቆጠሩ ወንድሞችና እህቶች ዓርብ ጠዋት ወደ ቼዝ ፊልድ የመጡ ልዑካንን ሞቅ ባለ ስሜት ሲቀበሉ
ልዑካኑ (አንዳንዶቹ የባሕል ልብስ ለብሰዋል) ስብሰባውን ሲከታተሉ
ከ352 ተጠማቂዎች መካከል ሁለቱ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ሳሙኤል ኸርድ የሁለተኛውን ቀን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ
ልዑካኑ ፓርክ እየጎበኙ ፎቶግራፍ ሲነሱ
ወንድሞቻችን በ19ኛው ክፍለ ዘመን የነበረውን የአሜሪካን ታሪክ ለማሳየት በተዘጋጀ ሰረገላ ሲሄዱ
ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች እሁድ ቀን በስብሰባው መደምደሚያ ላይ ሜዳው ላይ ሆነው