በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እህት ሄለን በጅ ብሬይል ኖትቴከር ስትጠቀም

መጋቢት 24, 2021
ዩናይትድ ኪንግደም

የአካል ጉዳተኛ መሆኗ በመታሰቢያው በዓል ዘመቻ ከመካፈል አላገዳትም

የአካል ጉዳተኛ መሆኗ በመታሰቢያው በዓል ዘመቻ ከመካፈል አላገዳትም

በኤድንበርግ፣ ስኮትላንድ የምትኖረው ሄለን በጅ የተባለች የይሖዋ ምሥክር ዓይነ ስውር ናት። በዓለም አቀፉ ወረርሽኝ ምክንያት በተጣሉት ገደቦች የተነሳ እንደ ሌሎቹ የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉ እህት ሄለንም በአገልግሎት ስትካፈል ሰዎችን በአካል ሄዳ ማነጋገር አትችልም። ይህ መሆኑ ግን በኢየሱስ ሞት መታሰቢያ በዓል ላይ ሰዎችን ለመጋበዝ በሚደረገው ዘመቻ ሙሉ ተሳትፎ እንዳታደርግ አላገዳትም።

እህት ሄለን ለሰዎች በምትልካቸው ደብዳቤዎች ላይ ልታካትት ያሰበችውን ሐሳብ መጀመሪያ በብሬይል ኖትቴከር አማካኝነት ትጽፋለች። “ኖትቴከር ለእኔ እንደ እርሳስና ወረቀት ነው” ብላለች። ከዚያም እህት ሄለን የጻፈችውን የብሬይል ማስታወሻ ተጠቅማ የደብዳቤዋን ሐሳብ ለእህቷ ልጅ እየነገረች ታስጽፋታለች።

በብሬይል የተዘጋጀው የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ

እህት ሄለን፣ እናቷም ሆኑ አያቷ የይሖዋ ምሥክሮች ስለነበሩ የመታሰቢያው በዓል ከልጅነቷ ጀምሮ ትልቅ ቦታ የምትሰጠው ክንውን ነው። እህት ሄለን ሰዎችን ለመታሰቢያው በዓል መጋበዝ ምንጊዜም በጉጉት የምትጠብቀው ነገር እንደሆነ ገልጻለች። እንዲህ ብላለች፦ “የመታሰቢያውን በዓል የማከብረው ለ70ኛ ጊዜ ነው። በየዓመቱ የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ በብሬይል ሲደርሰኝ በጣም ደስ ይለኛል። ስለ ስብሰባው ዝርዝር መረጃ ለማግኘት መጋበዣውን በደንብ አነበዋለሁ። ከዚያም እነማንን እንደምጋብዝ አስባለሁ።”

በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ታማኝ ክርስቲያኖች፣ ያሉበት ሁኔታ ምንም ይሁን ምን በፍቅር ተነሳስተው ሰዎችን ቅዳሜ፣ መጋቢት 27, 2021 ለሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ይጋብዛሉ።—ሉቃስ 22:19