በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቲያቺቭ፣ ዩክሬን ስደተኞችን ለመቀበል የተዘጋጀ የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ

መጋቢት 8, 2022
ዩክሬን

ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 1 | በዩክሬን ቀውስ ቢከሰትም የወንድማማች ፍቅር ታይቷል

ወቅታዊ መረጃ ቁጥር 1 | በዩክሬን ቀውስ ቢከሰትም የወንድማማች ፍቅር ታይቷል

በማሪዮፖል፣ በካርኪቭ፣ በሆሶትሜል እና በሌሎች ከተሞች የሚኖሩ ወንድሞቻንና እህቶቻችን በዩክሬን እየደረሰ ባለው የቦምብ ፍንዳታ የተነሳ ከባድ መከራን እየተጋፈጡ ነው። አንዳንዶች በምድር ቤት ወይም በመደበቂያቸው ከአንድ ሳምንት በላይ ለመቆየት ተገድደዋል። ያላቸው ምግብ እያለቀ ነው፤ ከዚህም ሌላ በኤሌክትሪክ ኃይል እጦት ላይ የኢንተርኔትና የሞባይል አገልግሎት ችግር ሲጨመር ከወንድሞቻችን ጋር መረጃ መለዋወጥ አስቸጋሪ ሆኗል።

በጣም የሚያሳዝነው ሚርኖህራድ ከተማ ውስጥ በጉባኤ ሽማግሌነት የሚያገለግለው የ28 ዓመቱ ወንድም ዲሜትሮ ሮዝዶርስኪ ፈንጂ በመርገጡ ሕይወቱ አልፏል። የሚወዱትን ሰው በሞት ላጡትና ከባድ የቦምብ ፍንዳታ በሚደርስባቸው አካባቢዎች ለሚኖሩ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንጸልያለን።—2 ተሰሎንቄ 3:1

በኦቭሩች፣ ዩክሬን የሚገኝ አንድ የስብሰባ አዳራሽ በቦምብ ፍንዳታ ወቅት ከባድ ውድመት ደርሶበታል

እስከ መጋቢት 7, 2022 ድረስ ከዩክሬን የሚከተለው አጠቃላይ ሪፖርት ደርሶናል፦

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 2 አስፋፊዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል

  • 8 አስፋፊዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 20,617 አስፋፊዎች ቤታቸውን ጥለው አገሪቱ ውስጥ አንጻራዊ ሰላም ወዳለባቸው ቦታዎች ሸሽተዋል

  • 25 ቤቶች ወድመዋል

  • 29 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 173 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 5 የስብሰባ አዳራሾች ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • 27 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ዩክሬን ውስጥ በሥራ ላይ ናቸው

  • 6,548 አስፋፊዎች በአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች እርዳታ አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው ቦታዎች ማረፊያ ማግኘት ችለዋል

  • 7,008 አስፋፊዎች ወደ ሌሎች አገሮች ሸሽተዋል፤ በዚያም የእምነት አጋሮቻቸው እርዳታ እያደረጉላቸው ነው

  • 1 የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽና 30 ገደማ የስብሰባ አዳራሾች ስደተኞችን ለመቀበል ተዘጋጅተዋል፤ እነዚህ አዳራሾች በምዕራባዊ ዩክሬን (ለምሳሌ በቼርኔቭትሲ፣ በኢቫኖ ፍራንኪቭስክ፣ በሊቪቭ እና በትራንስካርፓትያን ክልሎች) የሚገኙ ናቸው