በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በክዋዙሉ-ናታል ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ መጠነ ሰፊ ውድመት አስከትሏል

ሚያዝያ 25, 2022
ደቡብ አፍሪካ

በደቡብ አፍሪካ የደረሰ ከባድ ዝናብና የመሬት መንሸራተት አደጋ

በደቡብ አፍሪካ የደረሰ ከባድ ዝናብና የመሬት መንሸራተት አደጋ

ሚያዝያ 13, 2022 በደቡብ አፍሪካ በሚገኘው በክዋዙሉ-ናታል ግዛት ከባድ ዝናብ ጥሎ ነበር፤ በዚህም የተነሳ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፤ መጠነ ሰፊ ውድመትም ደርሷል። በአንዳንዶቹ አካባቢዎች በ24 ሰዓት ውስጥ 300 ሚሊ ሜትር ዝናብ ጥሏል። በብዙዎቹ አካባቢዎች ኤሌክትሪክና ውኃ ተቋርጧል። በርካታ መንገዶች ፈርሰዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • የአንዲት እህት ልጅ ግድግዳ ስለወደቀባት መጠነኛ ጉዳት ደርሶባታል

  • አንድ ወንድም ቤቱ በወደመበት ወቅት መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል

  • 27 ቤቶች ወድመዋል

  • 102 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 87 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 2 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ ሥራውን ለማስተባበር አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

  • የጉባኤ ሽማግሌዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቾች እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ክርስቲያኖች እርዳታ እያበረከቱ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ይሖዋ ንብረታቸውን ያጡትን ውድ ወንድሞቻችንን መርዳቱን እንደሚቀጥል እርግጠኞች ነን፤ ለወደፊቱ ጊዜ ያዘጋጀልንን ዘላለማዊ በረከቶች በጉጉት እንጠባበቃለን።—2 ቆሮንቶስ 4:18