መስከረም 16, 2019
ደቡብ አፍሪካ
ጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከመስከረም 6-8, 2019
ቦታ፦ ጆሃንስበርግ፣ ደቡብ አፍሪካ የሚገኘው ኤፍ ኤን ቢ ስታዲየም
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ሴሶቶ፣ እንግሊዝኛ፣ ዙሉ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 58,149
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 476
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,000
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ሃንጋሪ፣ ሆንግ ኮንግ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊ፣ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ማዳጋስካር፣ ብሪታንያ፣ ቦሊቪያ፣ ኡጋንዳ፣ እስራኤል፣ ኬንያ፣ ኮሪያ፣ ኮንጎ (ኪንሻሳ)፣ ዚምባብዌ፣ ዛምቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ጃፓን፣ ፊንላንድ፣ ፓራጓይ፣ ፔሩ
ተሞክሮ፦ ልዑካኑ ከጎበኟቸው ቦታዎች አንዱ የሆነው የአንበሳና የሳፋሪ ፓርክ ኃላፊዎች እንደዚህ ከብዙ ቋንቋና ባሕል የተውጣጡ ሰዎች ያለምንም ጭቅጭቅና ማጉረምረም ከጉብኝት አውቶቡስ ሲወርዱ አይተው እንደማያውቁ ተናግረዋል። ኃላፊዎቹ፣ ጎብኚዎቹ መመሪያ ለመከተልና ከሠራተኞቹ ጋር ለመተባበር ባሳዩት ፈቃደኝነት በጣም ተገርመው “እነዚህ ሰዎች በመምጣታቸው በጣም ተደስተናል!” በማለት ተናግረዋል።
የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች በደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን ማረፊያ ልዑካኑን ሲቀበሉ
ሁለት የአካባቢው እህቶች ከሁለት ልዑካን ጋር ሆነው የስብሰባውን መጋበዣ ሲያሰራጩ
የባሕል ልብስ የለበሱ ተሰብሳቢዎች ፎቶ ሲነሱ
ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ወቅት በፈገግታ ሲያጨበጭቡ
ከ476 ተጠማቂዎች መካከል አንዷ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም አንቶኒ ሞሪስ በምሳ እረፍቱ ወቅት ወንድሞችና እህቶችን ሰላም ሲል
በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ልዑካን የሆኑ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች ሕዝቡን ሰላም ሲሉ
ሦስት እህቶች በስብሰባው መደምደሚያ ላይ
በቀለማት ያሸበረቀ የአፍሪካ ልብስ የለበሱ የመዘምራን ቡድን አባላት በምሽቱ ፕሮግራም ላይ ሲዘምሩ