በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 20, 2019
ደቡብ ኮሪያ

ሶል፣ ደቡብ ኮሪያ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ሶል፣ ደቡብ ኮሪያ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከመስከረም 13-15, 2019

  • ቦታ፦ የኮሪያ ዓለም አቀፍ ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ ሶል፣ ደቡብ ኮሪያ

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ሩሲያኛ፣ ቻይንኛ ማንዳሪን፣ ኢንዶኔዥያኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ኮሪያኛ፣ ቬትናምኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 60,082

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 478

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 6,076

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማሌዥያ፣ ስካንዲኔቪያ፣ ብራዚል፣ ቼክ-ስሎቫክ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካዛክስታን፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ግሪክ፣ ፈረንሳይ፣ ፊንላንድ፣ ቬትናም

  • ተሞክሮ፦ ለልዑካኑ ምግብ ያቀረበ አንድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ የሆነው ቾይ ጂ ዉንግ እንዲህ ብሏል፦ “አንዱ የድርጅታችን ሠራተኛ በዚህ ሥራ የተነሳ የይሖዋ ምሥክሮች ምን ያህል ደግ እንደሆኑ እንዳስተዋለ ነግሮናል። እኔን ይበልጥ ያስገረመኝ ደግሞ ከሌላ አገር የመጡትም ሆኑ ኮሪያውያን የይሖዋ ምሥክሮች ቀደም ሲል ባይተዋወቁም እንኳ አንዳቸው ለሌላው ፍቅር ማሳየታቸው ነው። የቅርብ ጓደኛሞች እንደገና የተገናኙ ይመስል ነበር። በበርካታ ሃይማኖታዊ ፕሮግራሞች ላይ የተሳተፍኩ ቢሆንም የይሖዋ ምሥክሮች ያዘጋጁትን ይህን ፕሮግራም ልዩ ሆኖ አግኝቼዋለሁ።”

    የኡተም አስጎብኚ ኤጀንሲ የቦርድ አባል የሆነው አን ሶን ጁ እንዲህ ብሏል፦ “የይሖዋ ምሥክሮች ምን ያህል ደግ እንደሆኑና ምንጊዜም ፈገግታ እንደማይለያቸው ከተመለከትኩ በኋላ የእኛ ሠራተኞች የሆኑ የአውቶቡስ ሹፌሮች እንደ እነሱ እንዲሆኑ ለየት ያለ ማሳሰቢያ መስጠት እንደሚያስፈልግ ተሰማኝ። የይሖዋ ምሥክሮች እንዲህ ዓይነት ምግባር እንዲኖራቸው ያደረገውን ሚስጥር ለማወቅ ጓጉቼ ነበር፤ ሆኖም አብሬያቸው ስሠራ ከልባቸው እንደሚዋደዱና እንደሚከባበሩ እንዲሁም የሚያምኑበትን ነገር በተግባር እንደሚያውሉ ማስተዋል ቻልኩ። በሥራው የተካፈሉት የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉ ያለምንም ክፍያ በፈቃደኝነት እንደሚሠሩ ሳውቅ ተገረምኩ። አንዳቸው ሌላውን በትኩረት እንደሚያዳምጡና ምንጊዜም በፈገግታ ምላሽ እንደሚሰጡ መመልከቴ እኔም ምን ለውጥ ማድረግ እንዳለብኝ እንዳስብ አድርጎኛል። የሚቻል ከሆነ ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር በድጋሚ አብሬ ብሠራ ደስ ይለኛል።”

    የኤምቢሲ ሙንህዋ ብሮድካስቲንግ ስቴሽን ዴጃንግም ፓርክ የሥራ አመራር ዳይሬክተር የሆነው ኪም ጊዮ ሺክ እንዲህ ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል፦ “የይሖዋ ምሥክሮች ያዘጋጁት ይህ ፕሮግራም በጣም ደስ የሚል ነበር። የካቶሊክ እምነት ተከታይ ብሆንም እውነተኛ ክርስቲያኖች ምን ዓይነት ባሕርይ ሊኖራቸው እንደሚገባ በዝግጅቱ ላይ በደንብ አይቻለሁ። እኔም ሆንኩ የሥራ ባልደረቦቼ የይሖዋ ምሥክሮች ተባባሪና የተደራጁ መሆናቸውን አስተውለናል። ለሌሎች ደግነት ያሳዩ የነበረ ከመሆኑም ሌላ በግቢያችን ውስጥ ያለውን በጣም ትንሽ ነገር እንኳ ለመጠቀም ፈቃድ ይጠይቁ ነበር። እኔ ራሴ የይሖዋ ምሥክር የሆንኩ ያህል በጣም ኮርቼባቸዋለሁ።”

 

አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ ያሉ የተወሰኑ ወንድሞችና እህቶች ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካንን ሞቅ አድርገው ሲቀበሉ

ሁለት ልዑካን በአካባቢው ከሚኖሩ አንድ ወንድምና እህት ጋር የአደባባይ ምሥክርነት ሲሰጡ

በአካባቢው ያሉ አንዳንድ እህቶች ጠዋት ላይ ወደ ስብሰባ ቦታው የሚመጡ ልዑካንን ሲቀበሉ

ከሌላ አገር የመጣች እህት በአካባቢው ያለችን አንዲት እህትና ልጇን ፎቶግራፍ ስታነሳ

ብዙ አድማጮች በቅዳሜ ዕለት የቀረበውን ትምህርት ሲከታተሉ

አንድ ወንድም መስማትና ማየት ለተሳነው ወንድም የጥምቀት ጥያቄዎችን ሲያስተረጉምለት

ሦስት እህቶች ማስታወሻ በመያዝ ፕሮግራሙን በጥሞና ሲከታተሉ

ወንድም ስቲቨን ሌት የቅዳሜውን ዕለት የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ የነበሩ ስድስት የጥምቀት ገንዳዎችን የሚያሳይ ከላይ የተነሳ ፎቶግራፍ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በእሁዱ ስብሰባ መደምደሚያ ላይ አድማጮችን ሲሰናበቱ

በስብሰባው ላይ የተገኙ ባሕላዊ ልብስ የለበሱ አንዳንዶች ፎቶግራፍ ሲነሱ

በኮሪያ ቤቴል ውስጥ በተዘጋጀ የጉብኝት ፕሮግራም ላይ ልዑካኑ፣ ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋማቸውን የጠበቁ በርካታ ወንድሞችንና እህቶችን የሚያሳይ የፎቶግራፍ ስብስብ ሲመለከቱ

ለጉብኝት ከተመረጡት ቦታዎች በአንዱ ላይ ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን በአካባቢው ከሚኖሩ እህቶች ጋር ፎቶግራፍ ሲነሱ

ቡቼቹም የተባለውን የኮሪያ ባሕላዊ ጭፈራ ለልዑካኑ ያቀረቡት እህቶች ለፎቶግራፍ ቆመው