በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 28, 2020
ደቡብ ኮሪያ

በደቡብ ኮሪያ የተከሰተው እስከዛሬ ታይቶ የማያውቅ ከባድ ዝናብ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

በደቡብ ኮሪያ የተከሰተው እስከዛሬ ታይቶ የማያውቅ ከባድ ዝናብ ከፍተኛ ውድመት አስከተለ

ቦታ

ደቡብ ኮሪያ

የደረሰው አደጋ

  • በኮሪያ ኃይለኛ ዝናብ የሚጥልበት ወቅት የዘንድሮውን ያህል ለረጅም ጊዜ ቆይቶ አያውቅም

  • ያለማቋረጥ ሲጥል የነበረው ይህ ዝናብ አውዳሚ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 16 አስፋፊዎች ለጊዜው ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት

  • 30 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 19 የስብሰባ አዳራሾች ተጎድተዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የኮሪያ ቅርንጫፍ ቢሮ ሦስት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል

  • ጉዳት በደረሰባቸው ወረዳዎች ያሉ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችና የወረዳ የበላይ ተመልካቾች በአካባቢው ካሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ድጋፍ እያደረጉ ነው

  • ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶችና የስብሰባ አዳራሾች የማጽዳትና የመጠገን ሥራ እየተከናወነ ነው

ተሞክሮ

  • ከባድ ጉዳት ከደረሰባቸው አካባቢዎች አንዱ በሆነው በጉርዬ ከተማ የሚኖሩት ወንድም ሚን-ሶንግ ሊ እና ባለቤቱ ንብረታቸውን ሁሉ ትተው ከቤታቸው ለመፈናቀል ተገደዋል። ቤታቸው ሙሉ በሙሉ በጎርፍ ተጥለቅልቆ ነበር። የእርዳታ ሥራው ሲጀመር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው ተወካዮች የባልና ሚስቱን ቤት ያጸዱላቸው ከመሆኑም ሌላ አንዳንድ አስፈላጊ ቁሳቁሶችን አቅርበውላቸዋል። በተጨማሪም ቅዱስ ጽሑፋዊ ጥቅሶች በማካፈል አጽናንተዋቸዋል። እህት ሊ፣ እሷና ባለቤቷ የተደረገላቸውን እርዳታ በተመለከተ እንዲህ ብላለች፦ “ላደረጉልን እርዳታ በጣም አመስጋኝ ነኝ። ያከናወኑት ሥራ አስደናቂ ነው። የራሳቸው ቤት ቢሆን የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ አድርገውናል። በአደጋው ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣን አይካድም፤ ያገኘነው ነገር ግን ካጣነው በእጅጉ ይበልጣል።”

“የመጽናናት ሁሉ አምላክ” የሆነው ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በኮሪያ ያሉ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን መንከባከቡን ስለቀጠለ አመስጋኞች ነን።—2 ቆሮንቶስ 1:3, 4