በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 18, 2019
ደቡብ ኮሪያ

ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋም—የደቡብ ኮሪያ ወንድሞች የእምነትና የድፍረት ታሪክ

ክርስቲያናዊ የገለልተኝነት አቋም—የደቡብ ኮሪያ ወንድሞች የእምነትና የድፍረት ታሪክ

ከ1953 አንስቶ በኮሪያ የሚኖሩ ወጣት ወንድሞች ወታደራዊ አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ይታሰሩ ነበር። ከዚያን ጊዜ አንስቶ አቋማቸውን ለማላላት ፈቃደኛ ያልሆኑ ከ19,000 የሚበልጡ ወንድሞች በድምሩ 36,000 ዓመታት በእስር አሳልፈዋል። ሆኖም የካቲት 28, 2019 በእስር ላይ ከነበሩት ወንድሞች የመጨረሻው ተለቀቀ። ይሁንና እንዲህ ያለው ታሪካዊ ድል ሊገኝ የቻለው እንዴት ነው? የኮሪያ ወንድሞቻችን ያስመዘገቡትን አስደናቂ የእምነትና የድፍረት ታሪክ እስቲ እንመልከት።