የካቲት 23, 2021
ጃፓን
ሰሜን ምሥራቅ ጃፓን በከባድ የምድር መናወጥ ተመታ
ቦታ
ሰሜን ምሥራቅ ጃፓን፣ በዋነኝነት ፉኩሺማ እና ሚያጋ ግዛቶች
የደረሰው አደጋ
የካቲት 13, 2021 በምድር መናወጥ መለኪያ 7.3 የተመዘገበ የምድር መናወጥ ደርሶ ነበር፤ ይህም በአንዳንድ ቦታዎች ኤሌክትሪክ እና ውኃ እንዲቋረጥ አድርጓል። በ2011 በምድር መናወጥ መለኪያ 9.0 በደረሰ የምድር መናወጥ ከተመቱት ቦታዎች አብዛኞቹ በዚህኛው የምድር መናወጥም ተመትተዋል
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
11 አስፋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
በርካታ ወንድሞች ለጊዜው ኤሌክትሪክ እና ውኃ ተቋርጦባቸዋል
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
10 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
205 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
13 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
ጉዳት በደረሰበት አካባቢ ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች እና የጉባኤ ሽማግሌዎች ለአስፋፊዎች መንፈሳዊ ድጋፍ እየሰጡ ነው፤ ይህን የሚያደርጉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው
የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ዲፓርትመንት የመስክ ተወካዮች እንዲሁም የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች በእያንዳንዱ የስብሰባ አዳራሽና መኖሪያ ቤት ላይ የደረሰውን ጉዳት እያጣሩ ነው
ይሖዋ በዚህ የምድር ነውጥ የተጎዱትን እንዲያበረታቸው እንጸልያለን።—ፊልጵስዩስ 4:13