መስከረም 5, 2024
ጃፓን
ሻንሻን የተሰኘው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ ጃፓንን መታ
ነሐሴ 29, 2024 ሻንሻን የተሰኘው አውሎ ነፋስ በሰዓት 160 ኪሎ ሜትር ገደማ በሚደርስ ፍጥነት እየገሰገሰ በጃፓን የሚገኘውን የካጎሺማ አውራጃ መታ። በቶካይ፣ በኪዩሹ እና በካንቶ ክልሎች በሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በ48 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሳንቲ ሜትር በላይ ዝናብ ጥሏል። ይህን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት እና ጎርፍ የተነሳ መንገዶች እና ሕንፃዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከ120 በላይ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 8 ሰዎች ሞተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
የሞተ ወንድም ወይም እህት የለም
3 አስፋፊዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል
245 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
8 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
አውሎ ነፋሱ ጉዳት ባደረሰባቸው አካባቢዎች በርካታ የክልል ስብሰባዎችን ወደ ሌላ ጊዜ መግፋት ግድ ሆኗል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ሽማግሌዎች ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ላሉት መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው
እንዲህ ያሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ለከፍተኛ ሐዘን ቢዳርጉንም ‘ረዳታችን እና አጽናኛችን’ የሆነው ይሖዋ በሚሰጠን ድጋፍ እንበረታለን።—መዝሙር 86:17