ጥር 4, 2024
ጃፓን
በጃፓን የተከሰተው ከባድ የምድር ነውጥ ኖቶ የተባለውን ባሕረ ገብ መሬት መታ
ጥር 1, 2024 በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 7.6 የተመዘገበ የምድር ነውጥ በማዕከላዊ ጃፓን ኢሺካዋ ግዛት የሚገኘውን ኖቶ ባሕረ ገብ መሬት መታ። ዋናው የምድር ነውጥና ከዚያ በኋላ የተከሰቱት አነስተኛ ነውጦች በአካባቢው ባሉ ቤቶችና መንገዶች ላይ ከባድ ጉዳት አድርሰዋል። ከ33,000 በላይ ሰዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ተደርገዋል። በምድር ነውጡ ምክንያት 400 ገደማ የሚሆኑ ሰዎች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን 78 የሚያህሉ ደግሞ ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ የለም
1 ወንድም ቀላል ጉዳት ደርሶበታል
ከ150 የሚበልጡ ወንድሞችና እህቶች አካባቢውን ለቀው ወጥተዋል
2 ቤቶች ወድመዋል
7 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
ከ100 የሚበልጡ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
8 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል
የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ ተወካዮች አደጋ ወደደረሰበት አካባቢ ሄደው ወንድሞችን እንዲያበረታቱ ተልከዋል። በተጨማሪም የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያደረጉ ነው
ይሖዋ በጃፓን ላሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን “አስተማማኝ መጠጊያ” በመሆን በዚህ አስቸጋሪ ሁኔታ ሥር የሚያስፈልጋቸውን ማጽናኛና ብርታት እየሰጣቸው እንደሆነ እንተማመናለን።—መዝሙር 18:2