በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 10, 2019
ጃፓን

በጃፓን የደረሰ የጎርፍ አደጋ

በጃፓን የደረሰ የጎርፍ አደጋ

ነሐሴ 28, 2019 በጃፓን ኪዮሹ ግዛት የጣለው ከባድ ዝናብ ኃይለኛ ጎርፍ አስከትሏል። ወንዞች ሞልተው በመፍሰሳቸው እንዲሁም የመሬት መንሸራተት አደጋ ስጋት በመኖሩ የተነሳ ከ800,000 የሚበልጡ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ለመሄድ ተገደዋል። የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ 82 አስፋፊዎች መኖሪያቸውን ትተው እንደሄዱ ሪፖርት አድርጓል። በቅርብ የደረሱን ሪፖርቶች እንደሚያመለክቱት 40 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን አንድ የስብሰባ አዳራሽም ቀላል ጉዳት ደርሶበታል።

ቅርንጫፍ ቢሮው የተጎዱትን አስፋፊዎች ለመርዳት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል። የወረዳ የበላይ ተመልካቾች፣ የጉባኤ ሽማግሌዎችና አስፋፊዎች ለወንድሞቻችን የሚያስፈልገውን ቁሳዊና መንፈሳዊ እርዳታ እየሰጡ ነው። ወንድሞቻችን በፍቅር ተነሳስተው የእምነት ባልንጀሮቻቸውን ሲረዱ በመመልከታችን በጣም ተደስተናል።—2 ቆሮንቶስ 8:4