በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በደቡብ ምዕራብ ጃፓን የሚገኝ አንድ መንገድ በከባድ ማዕበል ሲመታ

ጥቅምት 10, 2019
ጃፓን

ታፓህ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ደቡባዊ ጃፓንን መታ

ታፓህ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ከባድ አውሎ ነፋስ ደቡባዊ ጃፓንን መታ

ታፓህ የተባለው አውሎ ነፋስ ከመስከረም 21 እስከ 23, 2019 በደቡባዊ ጃፓን ከባድ ነፋስና ዝናብ አስከተለ። አውሎ ነፋሱ አውሮፕላኖችና ባቡሮች ጉዟቸው እንዲሰረዝ ያደረገ ከመሆኑም ሌላ ከ30,000 በሚበልጡ ቤቶች ውስጥ ኤሌክትሪክ እንዲቋረጥ ምክንያት ሆኗል። በኦኪናዋና በክዩሹ የሚኖሩ ከ50 የሚበልጡ ሰዎች በአደጋው ቆስለዋል።

የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ ሪፖርት እንዳደረገው አምስት አስፋፊዎች የቆሰሉ ሲሆን አንዲት እህት ሆስፒታል ገብታ ሕክምና መከታተል አስፈልጓታል። ከ50 በላይ የሚሆኑ የወንድሞቻችን ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴውና ኃላፊነት ያላቸው ወንድሞች በአደጋው ለተጠቁ አስፋፊዎች ቁሳዊና መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት ጥረት እያደረጉ ነው። የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ አውሎ ነፋሱ ያስከተለውን ጉዳት እየተከታተለ እርዳታ መስጠቱን ይቀጥላል።

በጃፓን የሚኖሩ ወንድሞቻችን በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ በይሖዋ መታመናቸውን እንዲቀጥሉና መጽናኛ እንዲያገኙ እንጸልያለን።—መዝሙር 94:19