በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥቅምት 23, 2019
ጃፓን

ጃፓንን የመታው ሃጊቢስ የተባለ አውሎ ነፋስ

ጃፓንን የመታው ሃጊቢስ የተባለ አውሎ ነፋስ

ሃጊቢስ የተባለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የቀላቀለ ዝናብ ጥቅምት 12 እና 13, 2019 ኃይለኛ ጎርፍ በማስከተሉ ቢያንስ 77 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የኤሌክትሪክና የውኃ አገልግሎት ተቋርጦባቸዋል። የጠፉ ሰዎችን የመፈለጉ ሥራም እየተከናወነ ነው። ይህ አውሎ ነፋስ ከ1958 ወዲህ ጃፓንን የመታው እጅግ ኃይለኛው አውሎ ነፋስ እንደሆነ እየተነገረ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ከ889 ሚሊ ሜትር በላይ ዝናብ ዘንቧል።

በአደጋው ምክንያት የጠፋ ወይም ሕይወቱን ያጣ አንድም የይሖዋ ምሥክር የለም። ሆኖም አሥር አስፋፊዎች ቀለል ያለ ጉዳት ደርሶባቸዋል። በተጨማሪም ከ1,200 በላይ የሚሆኑ የወንድሞቻችን ቤቶች ተጎድተዋል። በድምሩ 23 የስብሰባ አዳራሾች ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን በጎርፍና በኃይል መቋረጥ ሳቢያ 3ቱን አዳራሾች በአሁኑ ወቅት ጨርሶ መጠቀም አይቻልም። በቶቺጊ የሚገኘው የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽም አነስተኛ ጉዳት ደርሶበታል።

በፉኩሺማ እና ናጋኖ ግዛቶች ውስጥ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል። የጉዳቱ ስፋት ሙሉ በሙሉ ሲታወቅ ደግሞ ተጨማሪ የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ሊቋቋሙ ይችላሉ። በአደጋው ለተጠቁ ወንድሞች ምግብና ውኃ እየቀረበላቸው ነው። በእነዚህ አካባቢዎች የሚያገለግሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾች መጽሐፍ ቅዱስን በመጠቀም ለወንድሞቻቸው ማበረታቻና ማጽናኛ እየሰጡ ነው።

ይሖዋ በዚህ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ ለወንድሞቻችን መጠጊያ እንደሚሆንላቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 142:5