በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

መስከረም 17, 2019
ጃፓን

ጃፓን ፋክሳይ በተባለው ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች

ጃፓን ፋክሳይ በተባለው ከባድ አውሎ ነፋስ ተመታች

ውቅያኖስ ላይ የተነሳው ፋክሳይ የተባለ ከባድ አውሎ ነፋስ መስከረም 9, 2019 ቶኪዮ፣ ጃፓን ደረሰ። ይህ ከባድ አውሎ ነፋስ በሰዓት 180 ኪሎ ሜትር ይጓዝ የነበረ ሲሆን በ580,000 መኖሪያ ቤቶች ላይ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲቋረጥ አድርጓል። ቢያንስ ሦስት ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል።

የጃፓን ቅርንጫፍ ቢሮ አንድም አስፋፊ ሕይወቱ እንዳላለፈ ሆኖም ጉዳት የደረሰባቸው ሰባት ወንድሞችና እህቶች እንዳሉ ገልጿል። እስካሁን ባለን መረጃ መሠረት ይህ አውሎ ነፋስ 895 የወንድሞቻችንን ቤቶች፣ 28 የስብሰባ አዳራሾችንና በቺባ የሚገኘውን የትላልቅ ስብሰባዎች አዳራሽ አውድሟል።

ቅርንጫፍ ቢሮው አውሎ ነፋሱ በወንድሞቻችን ላይ ምን ያህል ጉዳት እንዳደረሰ የሚያሳዩ መረጃዎችን ማሰባሰቡን ቀጥሏል። ‘ጽናትንና መጽናኛን የሚሰጠው አምላካችን’ ይሖዋ በዚህ አውሎ ነፋስ የተጎዱትን ወንድሞችና እህቶች መርዳቱን እንዲቀጥል እንጸልያለን።—ሮም 15:5