በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 23, 2020
ጆርጂያ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በጆርጂያኛ ወጣ

የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም በጆርጂያኛ ወጣ

እሁድ፣ ሰኔ 21, 2020 በቪዲዮ ኮንፈረንስ በተደረገ ልዩ ስብሰባ ላይ የተሻሻለው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ በጆርጂያኛ መውጣቱ ተገለጸ። የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ጄፍሪ ጃክሰን መጽሐፍ ቅዱሱ መውጣቱን አስቀድሞ በተቀረጸ ንግግር አማካኝነት አብስሯል። በአጠቃላይ 19,521 ሰዎች ፕሮግራሙን ተከታትለዋል። የዚህን መጽሐፍ ቅዱስ ኤሌክትሮኒክ ቅጂ ከ​jw.org ላይ ወዲያውኑ ማውረድ የሚቻልበት ዝግጅት ተደርጓል።

የተሻሻለውን የጆርጂያኛ መጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ለማጠናቀቅ አራት ዓመት ፈጅቷል። የትርጉም ቡድኑ አባል የሆነ አንድ ሰው እንዲህ ብሏል፦ “መጽሐፍ ቅዱሱ ቀለል ያለ አገላለጽ የሚጠቀም መሆኑ በየትኛውም ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎች ሐሳቡን እንዲረዱት ያስችላል። ብዙ ቤተሰቦች ይህን መጽሐፍ ቅዱስ አብረው በማጥናት እንደሚደሰቱ ተስፋ አደርጋለሁ።”

ሌላ ተርጓሚ ደግሞ “ግባችን ሁሉም አንባቢዎች የትምህርት ደረጃቸው ምንም ይሁን ምን፣ ነጥቡን በቀላሉ እንዲረዱት ማድረግ ነው” ብሏል።

ይህን ትክክለኛና ለመረዳት ቀላል የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም የሚጠቀሙ ሁሉ ይሖዋ በዚህ መልኩ ፍቅሩን ስለገለጸላቸው አመስጋኝ እንደሚሆኑ እርግጠኞች ነን።—ያዕቆብ 1:17