በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጣሊያን ውስጥ በኤሚሊያ-ሮማኛ ክልል በጎርፍ የተጥለቀለቀ የመኪና ማቆሚያ። ውስጠኛው ምስል፦ አንድ ወንድም በጎርፍ የተጥለቀለቀን መንገድ ሲያጸዳ

ግንቦት 24, 2023
ጣሊያን

ሰሜናዊ ጣሊያን በጎርፍ ተጥለቀለቀ

ሰሜናዊ ጣሊያን በጎርፍ ተጥለቀለቀ

በሰሜናዊ ጣሊያን በሚገኘው ኤሚሊያ-ሮማኛ ክልል የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል። ከግንቦት 15, 2023 አንስቶ ሁለት ቀን በማይሞላ ጊዜ ውስጥ እስከ 50 ሴንቲ ሜትር የሚደርስ ከፍተኛ ዝናብ ጥሏል። ከ40 በላይ ከተሞች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የጎርፍ መጥለቅለቁ እስካሁን ድረስ የ14 ሰዎችን ሕይወት እንደቀጠፈ ተረጋግጧል። ሺዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ጉዳት የደረሰበት ወይም ሕይወቱን ያጣ የይሖዋ ምሥክር የለም

  • 342 አስፋፊዎችና የቤተሰባቸው አባላት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 167 መኖሪያ ቤቶች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል። ከእነዚህ መካከል 72ቱ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል

  • 3 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የአካባቢው ሽማግሌዎች በአደጋው የተጎዱትን በመንፈሳዊ እያበረታቱና ቁሳዊ እገዛ እያደረጉላቸው ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚከታተል አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

ሁላችንም “የአምላክ ድንኳን ከሰዎች ጋር [የሚሆንበትን]” ጊዜ በናፍቆት እንጠባበቃለን፤ በዚያን ጊዜ የተፈጥሮ አደጋ ይደርስብኛል ብለን የምንሰጋበት አንዳች ምክንያት አይኖርም!—ራእይ 21:3, 4