ነሐሴ 4, 2023
ጣሊያን
በሰሜናዊ ጣሊያን እና በሲሲሊ ደሴት የተከሰተው ከባድ የአየር ሁኔታ
ከሐምሌ 22 እስከ 26, 2023 ድረስ ጣሊያን ሁለት የተለያዩ የአየር ሁኔታዎችን አስተናግዳለች። በሰሜናዊ ጣሊያን በሰዓት ከ120 ኪሎ ሜትር በላይ ፍጥነት ያለው ኃይለኛ አውሎ ነፋስ የተከሰተ ሲሆን 19 ሴንቲ ሜትር ገደማ ስፋት ያለው በረዶም ጥሏል። በተመሳሳይ ጊዜ ደግሞ በሲሲሊ ደሴት ከ330 በሚበልጡ አካባቢዎች ሰደድ እሳት ተከስቷል። በአካባቢው የተመዘገበው እስከ 47 ዲግሪ ሴልሸስ የደረሰው አዲስ ከፍተኛ የሙቀት መጠን እሳቱ በፍጥነት እንዲዛመት ምክንያት ሆኗል። በዚህም የተነሳ ብዙ ሕንፃዎች የወደሙ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጦባቸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መኖሪያቸውን ለቀው ወጥተዋል። አምስት ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በሰሜናዊ ጣሊያን የተከሰተው ኃይለኛ ነፋስ እና በረዶ
ከወንድሞቻችን እና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም
2 ወንድሞች ተጎድተዋል
36 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
242 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 የስብሰባ አዳራሽ ከባድ ጉዳት ደርሶበታል
12 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
በሲሲሊ ደሴት የተከሰተው ሰደድ እሳት
የሚያሳዝነው አንድ ባልና ሚስት ቤታቸው በእሳት ሲጋይ ሕይወታቸውን አጥተዋል
48 ወንድሞችና እህቶች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽ ወይም ቲኦክራሲያዊ ሕንፃ የለም
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው የሚገኙ የጉባኤ ሽማግሌዎች በሲሲሊ በተከሰተው ሰደድ እሳትና በሰሜናዊ ጣሊያን በጣለው በረዶ የቀላቀለ ዝናብ ለተጎዱ ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው
በሲሲሊ የሚደረገውን የእርዳታ እንቅስቃሴ እንዲያስተባብር 1 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል
በሲሲሊ አንድ ወንድማችንን እና አንዲት እህታችንን በሞት በማጣታችን ከልብ አዝነናል፤ በእነዚህ የተፈጥሮ አደጋዎች ለተጎዱት ሁሉ መጸለያችንን እንቀጥላለን። ይሖዋ በቅርቡ ሁሉንም ዓይነት መከራ የሚያስወግድበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—ራእይ 21:4