በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ነሐሴ 8, 2019
ፈረንሳይ

ፓሪስ፣ ፈረንሳይ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ

ፓሪስ፣ ፈረንሳይ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
  • ቀን፦ ከነሐሴ 2-4, 2019

  • ቦታ፦ በፓሪስ፣ ፈረንሳይ የሚገኘው ፓርክ ዴ ኤክስፖዚሲኦን ደ ፓሪኖር ቪልፓንት

  • ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ሩሲያኛ፣ ሮማንያኛ፣ ስፓንኛ፣ እንግሊዝኛ፣ ጀርመንኛ፣ ፈረንሳይኛ

  • ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 37,809

  • አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 265

  • ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,500

  • የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ሞልዶቫ፣ ብሪታንያ፣ ታሂቲ፣ ቺሊ፣ ኒው ካሊዶኒያ፣ ኢኳዶር፣ ካናዳ፣ ካዛክስታን፣ ኮት ዲቩዋር፣ ዛምቢያ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ግሪክ

  • ተሞክሮ፦ ስብሰባው በተካሄደበት ቦታ ከነበሩት ኃላፊዎች አንዱ በመኪናዎቹ ብዛት ምክንያት የተፈጠረውን ጭንቅንቅ ሲመለከት እንዲህ ብሏል፦ “እናንተ ሰዎች ጨርሶ አትበሳጩም እንዴ? በይሖዋ ምሥክሮች ስብሰባ ወቅት ማንም ሰው ክላክስ አልነፋም፣ አልተሳደበም፣ የብስጭት ፊት አላሳየም ወይም መስመሩን ጥሶ ለማለፍ አልሞከረም።”

    ልዑካኑ ባረፉበት ሆቴል ውስጥ የሚሠራ አንድ ሰውም እንዲህ ብሏል፦ “ብዙ ቡድኖችን አስተናግደናል፤ የእናንተ ድርጅት ግን ምንም ተወዳዳሪ የለውም። ሰዎቹ ደስተኞች ናቸው፤ በቦታው የሰፈነው መንፈስ በጣም ደስ ይላል።”

 

የአካባቢው ወንድሞችና እህቶች ልዑካኑን አውሮፕላን ማረፊያ ሄደው ሲቀበሉ

ወንድሞችና እህቶች በአደባባይ ምሥክርነት ሲካፈሉ፤ ታዋቂው አይፍል ታወር ከሩቅ ይታያል

ወንድሞችና እህቶች ከስብሰባው ቦታ ውጭ ሲጨዋወቱ

አንድ ባልና ሚስት በቅዳሜው ስብሰባ ላይ አብረው ሲጠመቁ

የታሂቲ ባሕላዊ ልብስ የለበሱ ልዑካን ስብሰባውን በጥሞና ሲከታተሉ

የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም አንቶኒ ሞሪስ የቅዳሜውን ስብሰባ የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ

ልዑካን ሆነው የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በእሁዱ ስብሰባ መደምደሚያ ላይ ተሰብሳቢዎቹን ሲሰናበቱ በቪዲዮ እየታዩ

ልዑካኑ ቤቴልን ሲጎበኙ አንድ ወንድም የፈረንሳይ ኬኮች የሚጋገሩበትን መንገድ ሲያሳይ