ኅዳር 8, 2019
ፊሊፒንስ
ማኒላ፣ ፊሊፒንስ—2019 “ፍቅር ለዘላለም ይኖራል”! ብሔራት አቀፍ ስብሰባ
ቀን፦ ከኅዳር 1-3, 2019
ቦታ፦ በማኒላ፣ ፊሊፒንስ የሚገኙት ሞል ኦቭ ኤዥያ አሪና እና ኤስ ኤም ኤክስ የስብሰባ ማዕከል
ፕሮግራሙ የተካሄደበት ቋንቋ፦ ታጋሎግ፣ እንግሊዝኛ
ከፍተኛ የተሰብሳቢዎች ቁጥር፦ 26,245
አጠቃላይ የተጠማቂዎች ቁጥር፦ 145
ከተለያዩ አገሮች የመጡ ልዑካን ብዛት፦ 5,397
የተጋበዙት ቅርንጫፍ ቢሮዎች፦ ማሌዥያ፣ ማዕከላዊ አውሮፓ፣ ማዳጋስካር፣ ምያንማር፣ ሰለሞን ደሴቶች፣ ስሪ ላንካ፣ ታይላንድ፣ ታይዋን፣ አውስትራሌዢያ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ካዛክስታን፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ጃፓን፣ ጣሊያን፣ ፈረንሳይ፣ ፓፑዋ ኒው ጊኒ
ተሞክሮ፦ የሞል ኦቭ ኤዥያ አሪና የደንበኞች አገልግሎት ኃላፊ የሆኑት ሮሄልዮ ሆሎንግባያን እንዲህ ብለዋል፦ “እስካሁን ካስተናገድናቸው ተሰብሳቢዎች መካከል የእናንተን ያህል ሥርዓታማ የሆነ ቡድን ገጥሞን አያውቅም። በአዳራሻችን ስለተሰበሰባችሁ በጣም ደስ ብሎናል።”
ብርጋዴር ጀነራል እና የደቡባዊ አውራጃ ፖሊስ ኃላፊ የሆኑት ኖላስኮ ባታን ደግሞ እንዲህ ብለዋል፦ “ሁሉም ልዑካን ወደ አዳራሹ የሚገቡት በሥርዓት ተሰልፈው ነው። እዚህ ሁሉም ነገር በጣም የተደራጀ ስለሆነ እኛ ራሱ አናስፈልግም።”
የማኒላ ሆቴል ምክትል የደህንነት ኃላፊ የሆኑት ትዮፊሎ ላቤ ለጉብኝት የሚሄዱትን ልዑካን እንዲከታተሉ ተመድበው ነበር። ለተወሰነ ጊዜ ያህል ልዑካኑን ከተከታተሉ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦ “የሆቴሉ ኃላፊዎች ‘የልዑካኑ የጉብኝት አደረጃጀት እንዴት ነበር?’ ብለው ከጠየቁኝ . . . ‘እጅግ በጣም ጥሩ የሚለው ራሱ አይበቃቸውም’ ብዬ ነው የምመልሰው። ቡድናችሁ በጣም የተደራጀ ነው።”
የፊሊፒንስ ወንድሞችና እህቶች በፊሊፒንስ ቤቴል ልዑካኑን ሲቀበሉ
ወንድሞችና እህቶች ከስብሰባው በፊት መጋበዣ ወረቀት ሲያሰራጩ
ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት አራት የቅርንጫፍ ቢሮው ተወካዮች ጋዜጣዊ መግለጫ ሲሰጡ
ተሰብሳቢዎቹ ከስብሰባው አዳራሽ ውጭ ሆነው
ከሌላ አገር የመጡ ልዑካንና የአካባቢው አስፋፊዎች አንድ ላይ ፎቶ ሲነሱ
ወንድሞችና እህቶች በስብሰባው ወቅት መዝሙር ሲዘምሩ
ቅዳሜ ዕለት ከተጠመቁት ወንድሞች መካከል ሁለቱ
የበላይ አካል አባል የሆነው ወንድም ማርክ ሳንደርሰን የቅዳሜውን የመደምደሚያ ንግግር ሲያቀርብ
ከሌላ አገር የመጡ የልዩ ሙሉ ጊዜ አገልጋዮች በስብሰባው የመጨረሻ ቀን ላይ ከወንድም ሳንደርሰን ጋር በመድረኩ ላይና ዙሪያ ቆመው
ምሽት ላይ በተዘጋጀው የመዝናኛ ፕሮግራም ላይ ወንድሞችና እህቶች ቲኒክሊንግ በመባል የሚታወቀውን የፊሊፒንስ ባሕላዊ ጭፈራ ሲያሳዩ