ኅዳር 23, 2023
ፊሊፒንስ
በደቡባዊ ፊሊፒንስ ከባድ ርዕደ መሬት ተከሰተ
ኅዳር 17, 2023 በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 6.7 የተመዘገበ ርዕደ መሬት በደቡባዊ ፊሊፒንስ አቅራቢያ በሚገኝ ባሕር ውስጥ ተከሰተ። ርዕደ መሬቱ የተከሰተው ከሚንዳናው ደሴት በስተ ደቡብ 26 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ነው። በዳቫዉ ክልል፣ በጀነራል ሳንቶስ ሲቲ እና በሳራንጋኒ ግዛት ውስጥ የመንግሥት ሕንፃዎችን፣ ትምህርት ቤቶችንና የገበያ ማዕከሎችን ጨምሮ የተለያዩ ሕንፃዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ብዙ ቤቶችም ተጎድተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
የሚያሳዝነው 1 እህት ሕይወቷ አልፏል
10 ወንድሞችና እህቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከእነዚህ መካከል አንዷ የወረዳ የበላይ ተመልካች ሚስት ስትሆን ሆስፒታል ብትገባም በአሁኑ ጊዜ ጥሩ ሁኔታ ላይ ትገኛለች
4 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል
4 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
2 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የእርዳታ ሥራውን የሚከታተል የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱት የእረኝነት ጉብኝት እያደረጉላቸው ነው
በዚህ ርዕደ መሬት ለተጎዱ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እንጸልይላቸዋለን፤ እንዲሁም እነሱን እየተንከባከቡ ያሉትን ልናመሰግን እንወዳለን። በዚህ ያልተረጋጋና ለመቋቋም አስቸጋሪ የሆነ ጊዜ ላይ ብንኖርም ዓለታችን ይሖዋ ለመጽናት የሚያስፈልገንን ጥንካሬ እንደሚሰጠን እንተማመናለን።—1 ሳሙኤል 2:2