በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሜትሮ ማኒላ፣ በታጊግ ሲቲ በእሳት የተቃጠሉት የወንድሞቻችን ቤቶች

ግንቦት 21, 2019
ፊሊፒንስ

በፊሊፒንስ የተነሳው እሳት ቤቶችን አወደመ

በፊሊፒንስ የተነሳው እሳት ቤቶችን አወደመ

መጋቢት 2019 ፊሊፒንስ ውስጥ ሳማር ደሴት ላይ በምትገኘው በካልባዮግ ሲቲ የተነሳው እሳት 128 ቤቶችን አቃጠለ። ባለፈው ወር በሉዞን ደሴት ላይ በምትገኘው በታጊግ ሲቲ ውስጥ የእሳት አደጋዎች ተከስተው ነበር። በድምሩ ሰባት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች በእሳቱ ወድመዋል። ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉት ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ ቤታቸው በአደጋው ባልተጎዳባቸው ሌሎች የይሖዋ ምሥክሮች ቤት አርፈዋል።

ቅርንጫፍ ቢሮው በአደጋው ለተጎዱት ምግብ፣ ውኃ እና አልባሳት የማቅረቡን ሥራ በማስተባበር በአፋጣኝ እርምጃ ወስዷል። በዚያ የሚገኙ ሽማግሌዎች በአደጋው ለተጎዱት እረኝነት ያደረጉላቸው ሲሆን የሚያስፈልጓቸውን ነገሮችም አሟልተውላቸዋል። ሁለት የእርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች፣ ከአካባቢ ንድፍና ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች ጋር በመተባበር የወንድሞቻችንን ቤት መልሰው ለመገንባት በዝግጅት ላይ ናቸው።

ይሖዋ በእሳት አደጋው ለተጎዱት ወንድሞቻችን መጠጊያቸው መሆኑን እንደሚቀጥል እንተማመናለን።—መዝሙር 62:8