ኅዳር 23, 2020
ፊሊፒንስ
ቫምኮ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ ቀደም ሲል በከባድ ዝናብ የተጎዱ አንዳንድ አካባቢዎችን መታ
ቦታው
ሉዞን
የደረሰው ጉዳት
ቫምኮ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ (በአካባቢው ዩሊሲስ ተብሎ ይጠራል) ኅዳር 11, 2020 ላይ በኬዞን ግዛት ውስጥ የምትገኘውን ፓትናኑንጋን የተባለች ቦታ ከመታ በኋላ በሉዞን በሚገኙ በርካታ አካባቢዎች ላይ ጉዳት አድርሷል
ቫምኮ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ በዚህ ዓመት ውስጥ ፊሊፒንስን ከመቱ አውሎ ነፋሶች መካከል 21ኛው ሲሆን በአገሪቱ ታሪክ ታይቶ የማያውቅ ጎርፍ አስከትሏል
ይህ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ የተከሰተው ከ2013 አንስቶ ፊሊፒንስን ከመቱት አውሎ ነፋሶች ሁሉ ከባድ የሆነው ጎኒ የተባለው አውሎ ነፋስ ከተከሰተና በሉዞን በሚገኙ አካባቢዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ካስከተለ ሁለት ሳምንት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ነው
በተከታታይ የጣለው ከባድ ዝናብ በትላልቅ ግድቦች ውስጥ ያለው የውኃ መጠን አደገኛ በሆነ ደረጃ ከፍ እንዲል አድርጓል። በዚህ የተነሳ ባለሥልጣናቱ የግድቡን ውኃ ለመልቀቅ የተገደዱ ሲሆን ይህም በአውሎ ነፋሱ ያልተጎዱ አካባቢዎች በጎርፍ እንዲጥለቀለቁ አድርጓል
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በጎርፉ ምክንያት ከ600 የሚበልጡ ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ከእነዚህ ቤተሰቦች መካከል አንዳንዶቹ ከፍ እያለ ከሚሄደው ውኃ ለመሸሽ ሲሉ እርዳታ እስኪደረግላቸው ድረስ ጣሪያ ላይ ለመውጣት ተገደዋል
አንድ ወጣት ወንድም የጠርሙስ ስብርባሪ ፊቱ ላይ ጉዳት አድርሶበታል። እሁን እያገገመ ነው
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
መጀመሪያ ላይ በደረሰን ሪፖርት መሠረት፦
ቢያንስ 6 የስብሰባ አዳራሾችና 1 የርቀት ትርጉም ቢሮ በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል
ቢያንስ 20 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
1 ቤት ሙሉ በሙሉ ፈርሷል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች ምግብ፣ ውኃና መጠለያ እንደ ማቅረብ ያሉትን መጀመሪያ ላይ የተደረጉ የእርዳታ ሥራዎች አስተባብረዋል
አንዳንድ ቤተሰቦች ወደ ቤታቸው ተመልሰው የማጽዳት ሥራ ጀምረዋል
3 አዳዲስ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች የእርዳታ እንቅስቃሴውን እያስተባበሩ ይገኛሉ
ወንድሞች የእርዳታ እንቅስቃሴው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ እንዲካሄድ ጥረት እያደረጉ ነው
ይሖዋ በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን እንደሚደግፍ እንተማመናለን። ሁሉም የይሖዋ ሕዝቦች የተፈጥሮ አደጋ ይደርስብኛል ከሚል ስጋት ነፃ ሆነው በሰላምና በደስታ የሚኖሩበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—መዝሙር 4:8