በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ትራሚ የመሬት መንሸራተት አስከትላለች፣ መንገዶች በጎርፍ ተወስደዋል እንዲሁም ቤቶች ወድመዋል

ጥቅምት 31, 2024
ፊሊፒንስ

ትራሚ የተባለችው አውሎ ነፋስ ፊሊፒንስን መታች

ትራሚ የተባለችው አውሎ ነፋስ ፊሊፒንስን መታች

ጥቅምት 21, 2024 ትራሚ a የተባለችው አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ ከፍተኛ ውድመት አስከትላለች። ትራሚ ወደ ሰሜኑ የአገሪቷ ክፍል ስትደርስ ይበልጥ የተጠናከረች ሲሆን በሰዓት እስከ 160 ኪሎ ሜትር የሚጓዝ ኃይለኛ ነፋስ አስነስታለች። ዶፍ ዝናብና ኃይለኛ ነፋስ የቀላቀለው ወጀብ፣ ጎርፍና የመሬት መንሸራተት በማስከተሉ በቤቶች፣ በመንገዶችና በመሠረተ ልማት አገልግሎቶች ላይ ጉዳት ደርሷል። ጉዳት በደረሰበት አካባቢ ከሚኖሩት ከስድስት ሚሊዮን ከሚበልጡ ሰዎች መካከል አንድ ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑት ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ቢያንስ 126 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • አንዲት እህት ሕይወቷን ማጣቷ የሚያሳዝን ነው

  • 747 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 7 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • 24 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 128 መኖሪያ ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 8 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

ሎውረል፣ ባታንጋስ፣ ፊሊፒንስ ውስጥ ወንድሞችና እህቶች የአደጋ ጊዜ እርዳታ ሥራ ሲያከናውኑ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው የሚገኙ የጉባኤ ሽማግሌዎች መንፈሳዊ ማበረታቻና ማጽናኛ ከመስጠት በተጨማሪ በአውሎ ነፋሱ ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ተግባራዊ እርዳታ ለማቅረብ የሚደረገውን እንቅስቃሴ በበላይነት እየተከታተሉ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ 5 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

ትራሚ ባስከተለችው ሞትና ውድመት በጣም አዝነናል። ሆኖም መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ የመሰሉ አደጋዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንደሚወገዱ በሰጠው ተስፋ እንጽናናለን።​—ኢሳይያስ 25:8

a ይህች አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ አውዳሚዋ ክሪስቲን የሚል ስያሜ ተሰጥቷታል