ሰኔ 22, 2021
ፊሊፒንስ
የይሖዋ ምሥክሮች አዲስ ዓለም ትርጉምን በቢኮል ቋንቋ አወጡ
በቢኮል ቋንቋ የተዘጋጀው አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሰኔ 20, 2021 በዲጂታል ፎርማት ወጣ። የፊሊፒንስ ቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል የሆነው ወንድም ዴንተን ሆፕኪንሰን በ97 ጉባኤዎች ለሚገኙ አስፋፊዎች በኢንተርኔት በተላለፈ ልዩ ስብሰባ ላይ ይህ መጽሐፍ ቅዱስ መውጣቱን አብስሯል።
አጭር መረጃ
የቢኮል ቋንቋን ከሚናገሩት 5.8 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች አብዛኞቹ የሚኖሩት በፊሊፒንስ በሚገኙት በሚከተሉት 5 ግዛቶች ውስጥ ነው፦ ሶርሶጎን፣ አልቤይ፣ ካማሬኔስ ሱር፣ ካማሬኔስ ኖርቴ እና ካታንዱዋንስ
ቢኮል ፊሊፒንስ ውስጥ ከሚነገሩት ቋንቋዎች በተናጋሪዎች ብዛት አምስተኛው ነው
ቢኮል በሚጠቀሙ ጉባኤዎች ውስጥ የሚያገለግሉ ከ5,800 የሚበልጡ አስፋፊዎች አሉ
በሥራው የተካፈሉት 2 የትርጉም ቡድኖች ሥራውን ለማጠናቀቅ 7 ዓመት ተኩል ፈጅቶባቸዋል
በሥራው ከተካፈሉት ተርጓሚዎች አንዱ እንዲህ ብሏል፦ “ቢኮል በርካታ ቀበልኛዎች ስላሉት አብዛኞቹ የቢኮል ተናጋሪዎች የሚረዷቸውን ቃላት ለመጠቀም ልዩ ጥረት አድርገናል።”
ሌላ ተርጓሚ ደግሞ እንዲህ ብሏል፦ “ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ግልጽና ቀላል ቋንቋ ስለሚጠቀም አንባቢዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችን በቀላሉ መረዳት እንደሚችሉ እርግጠኞች ነን።”
ተሻሽሎ የተዘጋጀው ሙሉው አዲስ ዓለም ትርጉም ፊሊፒንስ ውስጥ በሚነገሩት በሚከተሉት ስድስት ቋንቋዎችም ይገኛል፦ ሂሊጋይኖን፣ ሴብዋኖ፣ ታጋሎግ፣ ኢሎኮ፣ ዋራይ-ዋራይ እና ፓንጋሲናን።
ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በመውጣቱ የቢኮል ተናጋሪ ከሆኑ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ተደስተናል። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በርካታ ሰዎች ይሖዋን እንዲያወድሱትና ‘ለዘላለም ተደስተው እንዲኖሩ’ እንደሚረዳቸው እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 22:26