በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ታኅሣሥ 13, 2019
ፊሊፒንስ

የፊሊፒንስ የተወሰነ ክፍል በአውሎ ነፋስ ተመታ

የፊሊፒንስ የተወሰነ ክፍል በአውሎ ነፋስ ተመታ

ካሞራ ተብሎ የሚጠራው አውሎ ነፋስ (ፊሊፒንስ ውስጥ ትሶይ ይባላል) ታኅሣሥ 2, 2019 ደቡባዊ ሉዞን ውስጥ ቢኮል የሚባለውን ክልል መታ። በአውሎ ነፋሱ ምክንያት የተጎዳም ሆነ ሕይወቱን ያጣ አንድም የይሖዋ ምሥክር የለም፤ ሆኖም 108 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶች ከባድ ጉዳት 478 ቤቶች ደግሞ በከፊል ጉዳት ደርሶባቸዋል። ከዚህም በተጨማሪ 15 የስብሰባ አዳራሾች በአውሎ ነፋሱ ተጎድተዋል።

አውሎ ነፋሱ መጠነ ሰፊ ጉዳት በማስከተሉ የፊሊፒንስ ቅርንጫፍ ቢሮ ለወንድሞች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እንዲያደርጉ ስምንት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።

“በጭንቀት ቀን ይሖዋ ይስማህ። . . . ከቅዱሱ ስፍራ እርዳታ ይላክልህ” በማለት እንደጸለየው መዝሙራዊ እኛም በፊሊፒንስ የሚኖሩ ወንድሞቻችንን በጸሎት እናስባቸዋለን።—መዝሙር 20:1, 2