በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በማኒላ፣ ፊሊፒንስ ከሚገኙ በጎርፉ የተጎዱ የስብሰባ አዳራሾች መካከል ሁለቱ

ነሐሴ 5, 2024
ፊሊፒንስ

ጌሚ የተባለው አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ በሚገኙ ብዙ አካባቢዎች ጎርፍ አስከተለ

ጌሚ የተባለው አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ በሚገኙ ብዙ አካባቢዎች ጎርፍ አስከተለ

ሐምሌ 2024 መጨረሻ አካባቢ በምዕራብ ፓስፊክ ውቅያኖስ ጌሚ a የተባለ አውሎ ነፋስ ተፈጠረ። ይህ ከባድ አውሎ ነፋስ ፊሊፒንስን ባይመታም በአካባቢው ከተለመደው ይበልጥ ኃይለኛ ዝናብ እንዲዘንብ አድርጓል፤ ይህም በዋና ከተማዋ በማኒላ እና በአቅራቢያዋ ባሉ ቦታዎች መጠነ ሰፊ ጉዳት፣ የጎርፍ መጥለቅለቅና የመሬት መንሸራተት አስከትሏል። ወደ 4.8 ሚሊዮን ገደማ የሚሆኑ ሰዎች በተፈጥሮ አደጋው ጉዳት እንደደረሰባቸው ይገመታል። ከ600,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ ቢያንስ 39 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል የሞተ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 155 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል፤ አብዛኞቹ ግን አሁን ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል

  • 2 ቤቶች ወድመዋል

  • 11 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 42 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 11 የስብሰባ አዳራሾች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን የሚያስተባብሩ 6 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተቋቁመዋል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው ያሉ የጉባኤ ሽማግሌዎች በጎርፉ ለተጎዱ ሰዎች መንፈሳዊ ማበረታቻና ተግባራዊ እርዳታ እየሰጡ ነው

በስተ ግራ (ከላይ)፦ ወንድሞችና እህቶች የእርዳታ ቁሳቁሶችን ሲያዘጋጁ። በስተ ግራ (ከታች)፦ የታሸጉ ውኃዎችን ሲያዘጋጁ

በስተ ቀኝ፦ አንድ ወንድም በጎርፉ ለተጎዳች እህት የእርዳታ ቁሳቁስ ሲሰጥ

በዚህ አውሎ ነፋስ ለተጎዱት ሁሉ መጸለያችንን እንቀጥላለን፤ ‘የዘመናችን መተማመኛ’ የሆነው ይሖዋ ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ስለሚንከባከባቸው አመስጋኞች ነን።​—ኢሳይያስ 33:6

a ይህ አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ ካሪና ተብሎ ይጠራል።