በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ኖሩ የተባለው ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ ከፍተኛ የጎርፍ መጥለቅለቅ አስከትሏል

ጥቅምት 6, 2022
ፊሊፒንስ

ፊሊፒንስ ኖሩ በተባለው አውሎ ነፋስ ተመታች

ፊሊፒንስ ኖሩ በተባለው አውሎ ነፋስ ተመታች

መስከረም 25, 2022 ኖሩ (በፊሊፒንስ ካርዲንግ ተብሏል) የተባለው ዝናብ የቀላቀለ ኃይለኛ አውሎ ነፋስ በፊሊፒንስ፣ ኬዞን ግዛት በሚገኙት በፖሊሎ ደሴቶች ጉዳት አደረሰ። ቀጥሎም በአውሮራ ግዛት ጉዳት አደረሰ። አውሎ ነፋሱ በሰዓት 195 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ፍጥነት የነበረው ሲሆን አልፎ አልፎ ደግሞ በሰዓት ከ240 ኪሎ ሜትር በሚበልጥ ፍጥነት ይጓዝ ነበር። ኖሩ፣ በበርካታ ቤቶችና የመሠረተ ልማት አውታሮች ላይ ከባድ ጉዳት ከማድረሱም ሌላ ብዙ ቦታዎችን በጎርፍ አጥለቅልቋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ የለም

  • 180 ቤተሰቦች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 209 ቤቶች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 20 ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 22 ቤቶች ወድመዋል

  • 7 የስብሰባ አዳራሾች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • 2 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ተመድበዋል

  • በአካባቢው ያሉት የጉባኤ ሽማግሌዎች በአደጋው ጉዳት ለደረሰባቸው እረኝነት እያደረጉና የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች እያሟሉ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴው በሙሉ የሚካሄደው ከኮቪድ-19 ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

አውሎ ነፋሱ ጉዳት ያደረሰባቸው ወንድሞች ይሖዋን መጠጊያቸው አድርገዋል፤ እኛም ስለ እነሱ መጸለያችንን እንቀጥላለን።—መዝሙር 57:1