በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ጥር 2, 2020
ፊሊፒንስ

ፊሊፒንስ ፋንፎና በተባለ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ተመታች

ፊሊፒንስ ፋንፎና በተባለ ዝናብ የቀላቀለ አውሎ ነፋስ ተመታች

ፋንፎና የተባለው አውሎ ነፋስ (ፊሊፒንስ ውስጥ ኧርሱላ በመባል ይታወቃል) ታኅሣሥ 24, 2019 የምሥራቅ ሳማርን ክልል መትቷል። በአውሎ ነፋሱ ሕይወቱን ያጣም ሆነ የአካል ጉዳት የደረሰበት አንድም የይሖዋ ምሥክር የለም። ሆኖም 464 የይሖዋ ምሥክሮች ቤቶችና 6 የስብሰባ አዳራሾች ጉዳት ደርሶባቸዋል። የፊሊፒንስ ቅርንጫፍ ቢሮ በአደጋው በተጠቁት ደሴቶች ውስጥ ለሚኖሩ ወንድሞች መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ ለመስጠት አምስት የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎችን አቋቁሟል።

ፋንፎና በ2019 ፊሊፒንስን ከመቱት ዝናብ የቀላቀሉ አውሎ ነፋሶች 21ኛው ነው። ከዚህም ሌላ በአገሪቱ ደቡባዊ ክፍል በቅርቡ የመሬት መንቀጥቀጥ ደርሶ ነበር። በመሆኑም በአሁኑ ወቅት 18 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ፊሊፒንስ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው።

በፊሊፒንስ የሚኖሩ ወንድሞቻችን “እጅግ አፍቃሪና መሐሪ” በሆነው በአምላካችን በይሖዋ ታምነው በመጽናታቸው አመስጋኞች ነን።—ያዕቆብ 5:11